Saturday, 06 April 2019 15:28

“የባህር ወጥ” ቴአትር ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


በደራሲና አዘጋጅ እሱባለው የኔነህ ተደራሶ በኤርፆር የቴአትር ፕሮዳክሽን የሚቀርበው “የባህር ወጥ” ቴአትር መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር በድምቀት ይመረቃል፡፡ ይህ የሙሉ ሰዓት ቴአትር ትኩረቱን በወቅታዊው የሀገራችን ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮቸ ላይ አድርጎ ወቅታዊ የህዝባችን ጥላቻ፣ አለመግባባትና ቅራኔ በምን መልኩ በይቅርታ መታደስ እንዳበት በትዕይንቱ ማመላከቱን ደራሲና አዘጋጁ በቴአትሩ ላይ የማለዳ ኮከቦች ካፈራቸው አንዱ የሆነው ካሳሁን ቦጋለ፣ ግሩም አስፋው፣ ማቲዎስ ሽፈራው፣ አቤኔዘር ዓለማየሁ፣ ኤልሻዳይ ሚፍታህ፣ አሸናፊ ኃ/ማርያም፣ ብሩክ ሀብታሙና አማን ሎምባርዲያ ተሳትፈውበታል፡፡ በዕለቱ አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) ጌትነት እንየው፣ ፍቃዱ ከበደ፣ ሰርፀ ፍሬስብሀትና ሌሎችም በክብር እንግድነት ይታደማሉ ተብሏል፡፡ ኤርፆር የቴኤትር ፕሮዳክሽን ከዚህ ቀደም “የጊዮን ውርስ” የተሰኘ ቴአትር ለእይታ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

Read 5980 times