Saturday, 06 April 2019 14:58

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(4 votes)


                                 “በተማሪዎችና በመምህራን መካከል ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት የለም”
                                           

• በዩኒቨርሲቲው የፆታ ትንኮሳ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል
• ዩኒቨርሲቲው ችግር ያለባቸውን መምህራን አለመቆጣጠሩ ለችግሩ መባባስ ምክንያት ሆኗል ተብሏል
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱንና ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ሰሞኑን በዩኒቨርሲቲው ያደረገውን የመስክ ምልከታ አስመልክቶ በምክር ቤቱ በሰጠው ማብራሪያ ላይ እንደተገለፀው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሚታየው የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል ዋንኛው ምክንያት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ችግር ያለባቸውን መምህራን በተገቢው መንገድ ለመከታተልና ለመቆጣጠር አለመቻሉ ነው ብሏል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ማድረጉን ገልፆ በዚህም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መምራን በተማሪዎቻቸው ላይ የሚፈፀሙት የፆታ ትንኮሳ እየጨመረ መምጣቱን፣ ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት በተማሪና በመምህራን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለተማሪዎች ውጤት እየሰጡ መምጣታቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎችን ማግኘቱን አመልክቷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የፈተና ድግግሞሽ ከመኖረቸውም በላይ ተማሪዎች ከተማሩዋቸው ሞጁሎች ውጪ ፈተና እንደሚፈተኑ፣ ተማሪዎችን ከማብቃት ይልቅ ማባረርን እንደ መፍትሄ እርምጃ መወሰዱ ለትምህርት ጥራቱ ማሽቆልቆል በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲው በትምህርትም ሆነ በሌሎች የምርምር ዘርፎች ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲች ቀዳሚ ለማድረግ አምስት የፀጥታ ግብረ ሀይል አቋቁሞ እየሰራ ቢሆንም በግቢው ውስጥ የሚደረገው አስቸጋሪ የሆነ ብሄር ተኮር እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል ተብሏል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሚታየውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የትምህርት ጥራት ያለው ትምህርት አግንተውና ብቁ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ ትኩረት ሰትቶ መስራት እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡  

Read 6628 times