Saturday, 06 April 2019 14:55

የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ለባለዕድለኞች የሚተላለፍበት ቀን ተራዘመ

Written by  ሠላም ገረመው
Rate this item
(1 Vote)


የዕጣ አወጣጥ ስርአቱን ተከትሎ የተነሱ የወሰን ይገባኛል ጥያቄን መልስ ለመመለስ እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ መሪነት የተቋቋመው የወሰን እና የድንበር አጣሪ ቡድን ስራ አለመጠናቀቁ ላለመተላለፉ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የቤቶች እና ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢ/ር ሠናይት ዳምጤ ለአዲስ አድማስ  ገልፀዋል፡፡
በርካታ ሰዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይተላለፋል የተባለውን መረጃ በመያዝ ቢሯቸው ድረስ በመሄድ እየጠየቋቸው መሆኑን ኢ/ር ሠናይት ገልፀው በእኛ በኩል ያለውን ስራ አጠናቀናል የሚቀረው የኮሚቴው ውሳኔ በመሆኑ በዚህ ቀን ይተላለፋል ለማለት እቸገራለሁ” ብለዋል፡፡   እጣ የወጣላቸው አካላት ቤቶቹ የሚተላለፉበትን ቀን በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቀዋል - ሃላፊዋ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር መካከል ያለውን ወሰን እንዲያጠና የተቋቋመው ኮሚቴ ተግባሩን ባለማጠናቀቁ በሣምንቱ ለባለ እድለኞች ይተላለፋሉ ተብለው የነበሩ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤትን የማስተላለፊያ ጊዜ መራዘሙ ተገለፀ፡፡

Read 1877 times