Saturday, 30 March 2019 14:09

“ባዶ ሰው በባዶ ቤት” የግጥም መፅሐፍ ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የገጣሚ ሰዓሊና መምህር አንዱ ጌታቸው የተፃፉና የሙከራ ነክነት (experimental touch) ያላቸው ግጥሞች መድብል የሆነው “ባዶ ሰው በባዶ ቤት” መፅሀፍ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ መገናኛ ፓኖራማ ሆቴል ጎን በሚገኘው ቫምዳስ ሲኒማ ይመረቃል፡፡ በዕለቱ በርካታ የኪነ ጥበብ ስራዎች ለታዳሚ የሚቀርቡ ሲሆን ግጥሞች፣ ወጎች፣ የፍልስፍና እይታዎች፣ ዲስኩር፣ ወፍ በረር የመፅሐፍ ዳሰሳና ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎችና ሌሎችም ኪነ ጥበባዊ መሰናዶዎች ተደግሰዋል፡፡ በምርቃቱ ላይ መርዕድ ተስፋየየ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ ረድኤት ተረፈ፣ በፍቃዱ ባይለየኝ፣ ምስራቅ ተረፈና ሌሎችም ገጣሚያን ስራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የተለያዩ ድምፃዊያንና አጃቢዎቻቸው የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን እንደሚያደምቁት መምህርና ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ ገልጿል፡፡

Read 6093 times