Saturday, 30 March 2019 14:02

“ጎህ” የኪነ ጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


         በእውቁ የሁነት አዘጋጅና የመድረክ አስተባባሪ ሄኖክ የእታገኝ ልጅ እና እንዲሁም በእውቁ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ በየወሩ የሚሰናዳው “ጎህ” 3ኛው ዙር የኪነ ጥበብ ምሽት ረቡዕ የካቲት 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በዕለቱም ገጣሚያኑ ምንተስኖት ማሞ፣ ህሊና ደሳለኝ፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣ መስፍን ወ/ተንሳይ፣ ዮናስ ሀንገሶም፣ ሚኪያስ ምናሴና ፍቃዱ ጌታቸው ስራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ በጋዜጠኞቹ ፍቅር ይልቃልና እንዳልካቸው ዘነበ ወግ እንደሚቀርብ የገለፁት አዘጋጆቹ፣ ድምፃዊ መሳይ ተፈራ በመሶብ ባላዊ ባንድ ታጅቦ እንደሚያቀነቅንና ገጣ ካሳሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሹ) የአንድ ሰው ተውኔት እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ መድረኩ በገጣሚ በላይ በቀለ ወያ የሚመራ ሲሆን በዚህ ምሽት ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው 50 ብር እንደሆነም ተገልጿል፡፡

Read 794 times