Saturday, 30 March 2019 14:03

በ6.5 ሚ. ብር የተደራጀው ማክ ኢንተርቴይንመንት የመዝናኛ ኩባንያውን ዛሬ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


          የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ ለማዘመን በዘርፉ የተሰማራው ማክ ኢንተርቴይመንት የመዝናኛ ማዕከሉን ዛሬ ያስመርቃል፡፡ ማዕከሉ በ6.5 ሚሊዮን ተገነባና ቴክኖሎጂው ያፈራቸውን የሙዚቃ መሳሪያዎችን ከውጭ በማስመጣት ለሽያጭ የሚያቀርብበት ሲሆን ጥራት ያላቸው ሁሉም የሙዚቃ መሳሪያዎች፣ የስቱዲዮ እቃዎች ማለትም ማይኮች፣ ሄድ ሴቶች፣ ሚክሰሮች ለሙዚቃ ኮንሰርት የሚያገለግሉ መብራቶችና አጠቃላይ የመድረክ ማስጌጫዎችን እያስመጣ ያከፋፍላል፡፡
ማክ ኢንተርቴይንመንት ከዚህ ቀደምም ሁነቶችን በማዘጋጀት የተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎችን በማስጌጥ ለሙዚቃ ኮንሰርት አጠቃላይ ዝግጅቶችን በመስራትና በማስተባበር በመዝናኛ ዘርፍ ትልቅ አበርክቶ እንደነበረው የኩባንያው ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ደረጀ ዘነበ (ማክ) ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ዛሬ በሚመረቀው የመዝናኛ ማዕከሉ ስነ ሥርዓት ላይ የባህልና ቱሪዝም ኃላፊዎች፣ ትልልቅ የሙዚቃ ሰዎች በርካታ የኪነ ጥበቡ ማህበረሰብና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ባለቤቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

Read 6362 times