Saturday, 23 March 2019 15:07

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

 የአንበሳው ሹርባ

መቅደላ ጋራ ላይ - ያለፈው አንበሳ፣
ታላቁ ባለህልም - ያ ገናና ካሳ፣
ሽጉጡን ሲጠጣ፣ ሲቅመው ጥይቱን፣
ራሱን - ሲያጠፋ፣ በትኖት እውነቱን፣
ሀሳብና ትልሙን፣ ዕቅዱን ሲያፈሰው፣
ፅንስና ውጥኑን - ቃሉን ሲያላውሰው፣
ከላይ ተጎዝጉዞ፣ ተጎንጉኖ ከድኖት አክሊል
የነበረ፣
ሹሩባ - ውበቱ፣ እንግሊዝ - ያደረ፣
ውጥኑ እንደሞላ ህልሙ እንደሰመረ፣
መታሰሪያው ጉንጉን መጣልን እያለ፣
መንፈሴ ዘመረ፡፡
(ደረጀ በላይነህ)

Read 3155 times