Saturday, 23 March 2019 14:52

በናይጀሪያ ልጆቻቸውን የማያስተምሩ ወላጆች ሊከሰሱ ነው

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 የናይጀሪያ መንግስት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ልከው በማያስተምሩ ወላጆች ላይ ክስ እንደሚመሰርትና ቅጣት እንደሚጥል ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በናይጀሪያ ከ5 እስከ 14 አመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 10.5 ሚሊዮን ያህል ህጻናት ትምህርት እንደማይማሩ የጠቆመው ዘገባው፣ የአገሪቱ መንግስት የማይማሩ ህጻናትን ቁጥር ለመቀነስ በማሰብ ልጆቻቸውን በማያስተምሩ ወላጆች ላይ ክስ ለመመስረት መወሰኑን የአገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር አዳሙ አዳሙ እንዳስታወቁ አመልክቷል፡፡
በአገሪቱ በርካታ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚሆን በቂ ገንዘብ ስለሌላቸው ወደ ትምህርት ቤት ከመላክ ይልቅ በጎዳና ላይ ንግድ እንደሚያሰማሯቸው የጠቆመው ዘገባው፣ ትምህርታቸውን ከማይከታተሉት የአገሪቱ ህጻናት መካከል 60 በመቶ ያህሉ የሚገኙት የአሸባሪው ቡድን ቦኮ ሃራም በሚንቀሳቀስበት የአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ውስጥ እንደሆነም አመልክቷል፡፡ ዩኒሴፍ በቅርቡ ባወጣው መረጃ፤ ናይጀሪያ በአለማችን እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህጻናት ከሚገኙባቸው ቀዳሚዎቹ አገራት አንዷ ናት ማለቱንም አስታውሷል፡፡

Read 6474 times