Saturday, 23 March 2019 12:42

የሴቶች ወሲባዊ እርካታ ማጣት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(17 votes)

ወሲብ ስቃያማ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይንም ደግሞ ስሜት የለሽ ሊሆን ይችላል፡፡ አለበለዚያም እርካታን ማጣት ሊኖር ይችላል፡፡ ታድያ የዚህ ሁሉ ችግር ምንድው ብለን ስንጠይቅ የተለያዩ መልሶች ይኖሩታል። ምናልባትም ልጅ መውለድ አለመቻል እና የዚህ ውጤት የሚያስከትለው ስሜት ሊሆን ይችላል፡፡ ወሲብ በሚፈጸምበት ጊዜ ስሜቱን ለማጣጣም ከባድ ከሆነ እና ወሲብ ሲፈጸም የሚገኘውን መደሰት ማግኘት ካልተቻለ ቀጥሎ በዝርዝር የምንመለከታቸው የጤና ሁኔታዎች ውጤት ሊሆን ስለሚችል ሐኪምን ማነጋገር  ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ምናልባትም ያጡትን እርግዝና ከማግኘት ባሻገርም የደስታ ስሜትን እንዲሁም እርካታን ማግኘት ሊከተል ይችላል ይላል የሴቶች ጤናን የሚዘግበው ድረገጽ (Women Health)፡፡
HIV (ኤችአይቪ)የኤችአይቪ ቫይረስ፤
በሴቶች ጤና ገጽ የመጀመሪያው ችግር ተደርጎ የተቀመጠው ኤችአይቪ ነው፡፡ ኤችአይቪ በወንድም ይሁን በሴት በኩል ልጅ የመውለድ አቅምን ሊያዳክም የሚችል ሕመምን ሊያስከትል የሚችል መሆኑ አይካድም፡፡ ኤችአይቪ በአሁኑ ወቅት ጠንከር ያሉ መድሀኒቶችን በመውሰድ ከከባድ ሕመሞች ተመድቦ እንክብካቤ የሚደረግለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እያለ ልጅ መውለድ ስለሚፈልጉ በጤንነት እንዲኖሩ የሚያስችላቸው መንገድን ይከተ ላሉ፡፡ በትክክለኛው መንገድ ሐኪሞች የሚያማክሩ ዋቸውን እና የሚሰጡዋቸውን ትእዛዝ አክብረው የምክር አገልግሎቱንም ሆነ መድሀኒቶችን በመጠቀም የሚፈልጉትን ልጅ ለመውለድ በሚያስችል ሁኔታ ይኖራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ልጅ መውለድ ያለመቻልን በተመለከተም ተገቢውን ሕክምናና ክትትል በማድረግ መካንነትን የሚያስወግዱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ስለዚህም ወላጅ መሆን ይቻላል በሚ ለው መርህ መሰረት ጤናን ከጠበቁ በኤችአይቪ ልጅን ያለማግኘት ምክንያትነት ሊቀረፍ የሚችል ነው፡፡
ሴቶች ሊኖራቸው የሚገባው የወሲብ እርካታ ለምን አይኖራቸውም በሚል በቅድሚያ የተነሳውን ኤችአይቪ ዘለቅ ብሎ ልጆቹን መውለድ ብቻ ሳይሆን በልጆቹ ዙሪያ የሚወሰዱ እርምጃዎችን መመልከት ያሻል ከሚል ቀጣዩን ለንባብ ብለናል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ ቫይረስ በአዲስ የሚያዙ ሕጻናት ማለትም እድሜያቸው ከ(0-14)የሆኑት በውጭው አቆጣጠር ከ2010/ጀምሮ በ47% ቅነሳ ማሳየቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይህም ከ1995/ጀምሮ በግምት 1.6/ሚሊየን ያህል ህጻናት በቫይረሱ በአዲስ ይያዙ የነበረ ሲሆን የጸረ ኤችአይቪ ኤይድስ መድሀኒትን በመስጠቱ ረገድ በወጣው መመሪያ በመንተራስ ከ(2010-2015) እርጉዝ የሆነች ሴት ቫይረሱ በደምዋ ውስጥ ካለ እና ከወሊድ በሁዋላም በጡት ማጥባት ጊዜ ቫይረሱን ወደ ልጅዋ እንዳታስተላልፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ተደርጎአል፡፡
ከላይ በተጠቀሰው መንገድ የተለያዩ ድርጊቶች ቢኖሩም ነገር ግን በየአመቱ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ልጆች ቁጥር በማይታመን ሁኔታ ከፍ ብሎ ይገኛል። በ2016/ በአለም አቀፍ ደረጃ /24%/የሚሆኑ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ እርጉዝ ሴቶች ፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት ማግኘት ባለመቻላቸው ልጆቻቸውን መከላከል አልቻሉም፡፡ ስለሆነም በተጠቀሰው አመት ወደ 160.000/ የሚሆኑ ህጻናት በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን በቀን ሲለካ /438/ያህል ናቸው፡፡
በ2015/ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ በሚታይባቸው /21/ሀገራት /54% የሚሆኑ ህጻናት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሲሆን እነዚህ ህጻናትም በሕክምናው አሰራር በታዘዘላቸው ጊዜ ማለትም በተወለዱ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ምርመራ የተደረገላቸው መሆኑ ታውቆአል፡፡ በተከታዩ አመትም 1.8/ሚሊየን የሚሆኑ ህጻናት በደማቸው ኤችአይቪ ቫይረስ መኖሩ የተረጋገጠ ሲሆን 43% የሚሆኑት ፀረኤችኤቪ (ART) መድሀኒት የማግኘት እድሉ ነበራቸው፡፡ ነገር ግን ቫይረሱ በደማ ቸው ውስጥ ካለባቸው ህጻናት ግማሽ ያህሉ መድሀኒቱን ያላገኙ እና የህክምና እርዳታው እንዲደርሳቸው የሚጠብቁ ናቸው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በ2016ዓ/ም /120.000/ህጻናት ከኤችአይቪ ኤድስ ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ ሕመሞች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በአፍሪካ በደማቸው ውስጥ ኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸው አብዛኛዎቹ ህጻናት ይኖራሉ፡፡
ኤችአይቪ ኤይድስ በአፍሪካ ለአብዛኛዎቹ ታዳጊዎች ለመሞት ምክንያት ነው፡፡
AVERT/ በ2018 ዓ/ም ለንባብ እንዳበቃው ከሆነ የኤችአይቪ ኤይድስ ቫይረስ በደማቸው ያለባቸው ህጻናት ያላሰለሰ ክትትልና ተገቢውን የህክምና እርዳታ ቢያገኙ ረጅም እድሜና የተሟላ ሕይወትን ሊመሩ ይችላሉ፡፡
ስለዚህ ኤችአይቪ ለሴቶች የወሲብ እርካታ ማጣት እንደአንድ ምክንያት የሚወሰድና ልጅ በመውለድ በኩልም በሴቶችም ሆነ በወንዶች በኩል እንደ አንድ መሰናክል መቆጠሩን ለማስወገድ ከሚወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን የሚወለደው ልጅም ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግለት እንደሚገባ ነው የተለያዩ መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡  
የማህጸን በር ካንሰር፤
የማህጸን በር ካንሰር በተለይም በወጣት ሴቶች አእምሮ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ በ human papillomavirus (HPV) ምክንያት የሚከሰተው ይህ ችግር ለሴቶች እርካታን ማጣት ብቻም ሳይሆን እንደ አንድ ትልቅ ስጋት የሚቆጠር ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ ከ11.000/ ሴቶች በላይ ይህንን በሽታ ይጋፈጡታል፡፡ ብዙዎቹም በእድሜያቸው ልጆችን ማጥባት የሚችሉ ማለትም ያላረጁ ሴቶች ናቸው፡፡   
  በየዘመኑ ያላሰለሰ ምርምር እያደረጉ ለታማሚዎች መፍትሔን የሚሹ ባለሙያዎች መኖራቸው ብዙ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል አስችሎአል፡፡ ስለዚህም የማህጸን በር ካንሰርም አስቀድሞ ምርመራ በማድረግ ችግሩን መለየት ስለሚቻል ብዙዎች እየዳኑ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በእርግጥ በህክምናው ዘርፍ በሚደረጉ ምርመራዎች የሚወሰዱ መድሀኒቶች የተነሳ ልጅ ማርገዝ የማያስ ችሉ ምክንያቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ይህንን በሚመለከት ከሕክምና ባለሙያው ጋር በጥልቀት መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ምናልባትም መፍትሔው በቀላሉ ሊገኝ ወይንም ወደችግር የማይገባበት መንገድ ሊኖር ይችላል፡፡
ሌላው ከልክ በላይ መወፈርና መቅጠን ነው፡፡
ሴቶች ሊኖራቸው ከሚገባው በላይ ከልክ ያለፈ ክብደት ሲኖራቸው ልጅ የመውለድ እድላቸውን ያጠበዋል፤ ምናልባትም ቢረገዝም ካለጊዜው ሕይወት አልባ ሆኖ ሊቋረጥ ይችላል፤አለዚያም ሌላ የስነተዋልዶ ጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ በእርግጥ ወፍራም ሴቶች እርግዝናን ጭርሱንም ሊያገኙት አይችሉም ለማለት ሳይሆን ግን ይበልጥ ጤናማ የሚሆነው ክብደትን ቀንሶ ማርገዝ ሲቻል ነው፡፡ ወፍራም ሴቶች ክብደታቸውን ቀንሰው የሚያረግዙ ከሆነ በእርግጠኝነት ሕይወት ያለውን ልጅ ማለትም የእርግዝና ጊዜውን ጨርሶ በሰላም ሊወልዱ ይችላሉ፡፡  
ቅጥነትም በተመሳሳይ መንገድ በሴቶች ስነተዋልዶ ጤንነት ላይ ችግር ሊፈጥር የሚችል ነው፡፡ አንዲት ሴት በተፈጥሮ ከልክ በላይ ቀጭን ካልሆነች እና በተለያየ ምክንያት ክብደትዋ ከልክ በላይ ከወረደ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ በተለይም እርጉዝ ለመሆን የተወሰነ መጠን ያለው ክብደት ሊኖራት ይገባል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በከፍተኛ ሁኔታ ክብደትዋ የቀነሰ ሴት በእርግዝናዋ ጊዜ የተለያዩ ችግሮች ሊገጥሙዋት የሚችሉ ሲሆን በተለይም ጽንሱ እንዲጨናገፍ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በውፍረትም ይሁን በቅጥነት ምክንያት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሴቶች ወሲብ መፈጸምን ላይፈልጉት ይችላሉ፡፡

Read 19511 times