Sunday, 17 March 2019 00:00

የተክሉ ኡርጋ “ከፍሎ ሟች” ፊልም ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


      በገሳ ኢቨንት ኦርጋናይዘርና በአስተማሪው ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ፣ በአብዲሳ ምትኩ ተደርሶ በተክሉ ኡርጋ (ንጋት) የተዘጋጀው “ከፍሎ ሟች” ፊ ልም ማ ክሰኞ ከ ቀኑ 1 1፡00 ጀ ምሮ የ ፊልም ባለሙያዎች፣ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዓለም ሲኒማ እንደሚመረቅ የፊልሙ አዘጋጅ ተክሉ ኡርጋ ገለፀ፡፡ ድራማ ኮሜዲ ዘውግ ባለው በዚህ ፊልም ላይ በዋናነነት በአገራችን በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችና ህፀፆች እየተቀነሱ ይተቻሉ ተብሏል፡፡ የ95 ደቂቃ ርዝመት ባለው በዚህ ፊልም ላይ አንጋፋዎቹ ተዋንያን ፍቅርተ ደሳለኝ፣ አለማየሁ ታደሰ፣ ሄለን በድሉ ዓለማየሁ በላይነህ ቴዎድሮስ ወንድሙ (ኪንግ) እና ሌሎችም ወጣትና አንጋፋ ተዋንያን ተሳትፈውበታል ተብሏል፡፡ ከምርቃቱ በኋላ በተለያዩ የግልና የመንግስት ሲኒማ ቤቶችም
ለእይታ እንደሚበቃ ዳይሬክተሩ ተክሉ ኡርጋ ገልጿል፡፡

Read 4754 times