Sunday, 17 March 2019 00:00

“ኢትዮጵያ ዛሬና ነገ” የኪነጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚቀርበው “ኢትዮጵያ ዛሬና ነገ” ልዩ የኪነጥበብ ምሽት ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በምሽቱ ዲስኩር፣ ወግ፣ ግጥምና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርቡ ሲሆን፤ መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድና የሙዚቃ ተመራማሪ ሰርፀ ፍሬ ስብሃት ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ኤፍሬም ስዩም፣ አርቲስት ፈቃዱ ከበደ፣ በላይ በቀለ ወያ እና ህሊና ደሳለኝ በግጥሞቻቸው ምሽቱን ያደምቁታል ተብሏል፡፡ ዝግጅቱ በመሶብ ባህላዊ ባንድ እንደሚታጀብና የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ትኬቶቹን በጃፋር መጽሐፍት መደብር፣ በዮናስ መፃሕፍት መደብር፣ በአይናለም መጽሐፍት መደብር፣ በጣይቱ ሆቴልና ካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት ማግኘት እንደሚቻል ጋዜጠኛ ምስክር ጌታነው አስታውቋል፡፡
ርዕስ ፒዩር ኢንተ ሞርኒንግ በጐ አድራጐት ለህፃናቱ የመዝናኛና የምሳ ግብዣ አዘጋጅቷል

Read 4651 times