Monday, 18 March 2019 12:15

በጣሊያን ያልተከተቡ ህጻናት ት/ቤት መግባት አይችሉም ተባለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ያልተከተቡ ልጆችን ት/ቤት የላኩ ወላጆች ይቀጣሉ

       በጣሊያን አስፈላጊውን ክትባት በተሟላ ሁኔታ ያልተከተቡና ስለመከተባቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሌላቸው ህጻናት ትምህርት ቤት መግባት እንደማይችሉ የአገሪቱ ፓርላማ ወስኗል፡፡
በአገሪቱ ከሰሞኑ በጸደቀው ህግ መሰረት፤ እስከ ስድስት አመት ዕድሜ ያላቸውን ያልተከተቡ ህጻናት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት የላኩ ጣሊያናውያን ወላጆች እስከ 560 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በጣሊያን ክትባት ግዴታ እንዲሆን በቀረበው ሃሳብ ላይ ለወራት ክርክር ከተደረገበት በኋላ፣ ከሰሞኑ ህግ ሆኖ መጽደቁን የጠቆመው ዘገባው፣ ህጉን ማውጣት ያስፈለገው ከ80 በመቶ በታች የሆነውን የአገሪቱን የክትባት ሽፋን ለማሳደግ ነው መባሉንም አመልክቷል፡፡

Read 1466 times