Sunday, 17 March 2019 00:00

በሶርያ 3 ሺህ የአይሲስ ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸው ተነገረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በሶርያ ምስራቃዊ አካባቢ በምትገኘው ባጉዝ የተባለች መንደር ባለፈው ማክሰኞ ብቻ 3 ሺህ ያህል የአሸባሪው ቡድን የአይሲስ አባላትና ታጣቂዎች በአሜሪካ ለሚደገፈው የሶርያ ዲሞክራቲክ ጦር እጃቸውን መስጠታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ ጦር ባለፉት ሳምንታት በአይሲስ ይዞታ ስር በምትገኘው መንደር ከፍተኛ የአየር ድብደባ ሲያደርጉ መቆየታቸውንና ብዙዎችን መግደላቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ ታጣቂዎቹ እጃቸውን እንዲሰጡ ቀነ ገደብ በተቀመጠላቸው መሰረት እጅ መስጠታቸውን አመልክቷል፡፡
ባለፈው ሰኞ ጦሩ ለ20 ጊዜ ያህል የአይሲስ ከባድ መሳሪያዎችንና ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ምሽጎችን ማውደሙንና 40 ያህል የአይሲስ ታጣቂዎችን መግደሉንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

Read 1078 times