Sunday, 10 March 2019 00:00

“ሙላ ነስረዲን” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)


         በደራሲና ጋዜጠኛ ግሩም ተበጀ የተሰናዳውና የቱርካዊውን የሙላ ነስረዲንን ዘመን አይሽሬ ጨዋታዎች ከጥንት እስከ ትላንት ጠዋት የሚዘክር
“ሙላ ነስሩዲን” የተሰኘ መጽሐፍ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ መጽሐፉ የሙላ ነስሩዲንን ማንነት፣ ዓለምአቀፍ ሰብዕናውን፣ ከጥንት እስከ ዛሬ ተሻግረው ስለመጡትና የ800 ዓመታት እድሜ ስላስቆጠሩት ጨዋታና ቀልዶቹ እንዲሁም ዓለም ስለሚሻማበት የዜግነቱና የትውልዱ ጉዳይ እንደሚተነትን ጋዜጠኛና ደራሲ ግሩም ተበጀ በመግቢያው ላይ በስፋት አቅርቦታል፡፡ በ170 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ120 ብርና በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 7401 times