Saturday, 09 March 2019 00:00

“የተቆለፈበት ቁልፍ” መፅሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


          ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በዶ/ር ምህረት ደበበ “የተቆለፈበት ቁልፍ” መፅሐፍ ላይ በብሔራዊ ቤተ
መዛግብትና ቤተ መፃህፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡
      በመፅሐፉ ላይ ስነ ልቦናዊ ሂስና ጥናታዊ ፅሁፍ የሚቀርብ ሲሆን ለውይይት የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የ3ኛ ዲግሪ ተማሪና በዲላ ዩኒቨርሲቲ የስነ ፅሁፍና የፎክሎር መምህር የሆኑት አቶ እንግዳወርቅ እንድሪስ ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ ታውቋል፡፡ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡

Read 846 times