Saturday, 26 May 2012 12:58

“ጋጋሪው” ፊልም ነገ እና ከነገ ወዲያ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ሳታፈቅረኝ” ፊልም ይመረቃል

በኬብሮን ፊልም ፕሮዳክሽን ከኢንስታይል ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር በመሆን የሰራው “ጋጋሪው” የዘጠና ደቂቃ አስቂኝ የፍቅር ፊልም ነገ እና ከነገ ወዲያ ይመረቃል፡፡ ብሩክ ሞላ ፅፎ ባዘጋጀውና ለዝግጅት ስምንት ወራት በፈጀው ፊልም ሰይፈ አርአያ፣ መለሰ ወልዱ፣ ብሩክ ፋንቱ፣ ዊንታና ባራኺ፣ አላዛር ሳለልኝ፣ ዮሴፍ ጌታቸው፣ እስጢፋኖስ ባህሩ፣ ፀሃይ ኃይለማርያም እና ሌሎች ተውነውበታል፡፡ በፊልሙ የነገ ምርቃት የአዲስ አበባና የክልል ከተሞች ሲካተቱ ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በልዩ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ይመረቃል፡፡

በተመሳሳይ ዜና አልማዝ ፊልም ፕሮዳክሽንና መልቲ ሚዲያ ያዘጋጀው “ሳታፈቅረኝ” ፊልም ሰኞ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ይመረቃል፡፡ በአልጊቱ ታምራት የተፃፈውን ፊልም ስንታየሁ ንጉሴ አዘጋጅቶታል፡፡ በ112 ደቂቃ ፊልሙ ላይ አበባው መላኩ፣ ሕይወቴ አበበ፣ አልጊቱ ታምራት፣ አስራት ታደሰ፣ ቤዛን ግርማይ እና ሌሎችም የተወኑበት ሲሆን ዝግጅቱም ሁለት ዓመት ወስዷል፡፡

 

 

Read 966 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 13:01