Print this page
Sunday, 03 March 2019 00:00

5ኛው ጉማ አዋርድ መጋቢት 17 ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ይሆናል

በኢትዮ ፊልምና በዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነመዋ በየዓመቱ የሚዘጋጀው 5ኛው “ጉማ የፊልም ሽልማት” መ ጋቢት 1 7 ቀ ን 2 011 ዓ .ም ከ ቀኑ 1 1፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ የዘንድሮው የህይወት ዘመን ተሸላሚው ፕ/ር ኃይሌ ገሪማ መሆኑም በመገለጫው ታውቋል፡፡
አዘጋጆቹ ከትላንት በስቲያ ምሽት በቤስት ዌስተርን ሆቴል በሰጡት መግለጫ በ2010 የተሰሩ 61 ያህል ፊልሞች ተመዝግበው መስፈርቱን ያሟሉ 25 ፊልሞች ብቻ ለውድድር መቅረባቸውን አዘጋጁ ዮናስ ብርሃነመዋ ገልፆ፣ ፊልሞቹ በኢዮሃ ሲኒማ ለዳኞች ዕይታ ከቀረቡ በኋላ ለመጨረሻው ዙር ያለፉ እጩዎች  ረጣቸውን ተናግሯል፡፡በ16ቱም ዘርፎች አሸናፊ የሆኑት ፊልሞችና ሞያተኞች በመጋቢት 17 ለሽልማት የሚቀርቡ ሲሆን በበደሌ ስፔሻል ስፖንሰርነት በሚካሄደው በዚህ የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ለመታደም ወንዶች በሱፍ ሴቶች በባህል አልባሳት መምጣት የግድ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Read 4407 times