Wednesday, 27 February 2019 13:10

“ሥዕላዊ ቅኔ” የስዕል ትርኢት ለ2 ወራት ይጐበኛል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

28ኛው ዙር የጋለሪያ ቶሞካ የስዕል ትርኢት “ሥዕላዊ ቅኔ” በሚል ርዕስ ትላንት ምሽት፣ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው ቶሞካ ጋለሪ
ተከፈተ፡፡ሰዓሊ ሚሊዮን ብርሃኔ የተጠበበችባቸው በርካታ ስዕሎች ለእይታ የበቁበት የስዕል ትርኢቱ፤ለቀጣይ ሁለት ወራት ለጉብኝት ክፍት ሆኖ
እንደሚቆይና በተከፈተ በአንድ ወሩ በስዕል አሳሳል ዘይቤዋና በስራዎቿ ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ የጋለሪያ ቶሞካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነብዩ
ግርማ ገልጸዋል፡፡

Read 5043 times