Saturday, 26 May 2012 12:50

“ፍኖተ-ጥበብ” ሰኞ ይቀርባል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በደብረ ዘይት ከተማና አካባቢዋ ሥነ ፅሁፍ አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ሆራ ቡላ” የሥነፅሁፍ ማህበር ከነገ ወዲያ ሰኞ “ፍኖተ ጥበብ” የተሰኘ ጥበባዊ ዝግጅት እንደሚያቀርብ ገለፁ፡፡ ከቀኑ 7፡30 በህይወት ሲኒማ የኪነጥበብና ባህል ማዕከል ትንሿ አዳራሽ የሚቀርበው ዝግጅት የክብር እንግዳ የ”ሰው ለሰው” የቴለቪዥን ድራማ ተባባሪ ደራሲ እና ምክትል አዘጋጅ መስፍን ጌታቸው ነው፡፡

በዚሁ ጊዜ ከሚቀርቡት ልዩ ልዩ የኪነጥበባት ድግሶች በተጨማሪ በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው ደራሲና ጋዜጠኛ ስብሃት ለአብ ገብረእግዚአብሄር፣ ደራሲና ተርጓሚ ማሞ ውድነህ እና እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይዘከራሉ፡፡

 

 

 

Read 1012 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:57