Sunday, 24 February 2019 00:00

በአማራ ክልል በሶስት ሣምንት ውስጥ ከ45ሺህ በላይ ዜጐች ተፈናቅለዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)


ባለፉት ሶስት ሣምንታት በማዕከላዊ ጐንደር ተፈጥሮ በነበረ ግጭትና አለመረጋጋት ከ45ሺህ በላይ ዜጐች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ያስታወቀ ሲሆን፤ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስንዝቧል፡፡
እነዚህ የተፈናቀሉትን ከ45ሺህ በላይ ዜጐች ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግስት 35 ሚሊዮን ብር መድቦ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ከሚፈለገው አጠቃላይ እርዳታ አንፃር በቂ አይደለም ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ በአማራ ክልል ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጐች ቁጥር ከ80ሺህ በላይ መሆኑም በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡
ሁሉም ዜጐች የተፈናቀሉት በክልሉና ከክልሉ ውጪ በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት መሆኑን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ መንግስት ተፈናቃዮቹን መልሶ በማቋቋም ተግባር ጠንክሮ እንዲሠራ አስገንዝቧል፡፡

Read 5715 times