Saturday, 16 February 2019 15:04

በአሜሪካ ለፍቅረኞች ቀን 20.7 ቢሊዮን ዶላር ያህል ወጪ ተደርጓል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በተለምዶ ቫላንታይንስ ዴይ በመባል የሚጠራው የፍቅረኞች ቀን ከትናንት በስቲያ በተለያዩ አገራት የተከበረ ሲሆን፣ አሜሪካውያን ከፍቅረኞች ቀን ጋር በተያያዘ በድምሩ 20.7 ቢሊዮን ዶላር ያህል ወጪ ማድረጋቸውንና ይህም በታሪክ ከፍተኛው ወጪ መሆኑን ፎርብስ መጽሄት ዘግቧል፡፡
አሜሪካውያን በሃሙሱ የቫላንታይንስ ዴይ ለፍቅረኞቻቸው ውድ ጌጣጌጦችን፣ አበባዎችን፣ ከረሜላዎችንና የመዋቢያ ዕቃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን ለመስጠትና ልዩ የራት ግብዣ ለማድረግ ያወጡት አጠቃላይ ወጪ ከአምናው የ6 በመቶ ያህል ጭማሪ ማሳየቱን ዘገባው አመልክቷል፡፡
ባለፈው ሃሙስ አሜሪካውያን ለፍቅረኞቻቸው ወጪ ካደረጉት 20.7 ቢሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ መካከል 18 በመቶው ወይም 3.9 ቢሊዮን ዶላር ያህሉ ለወርቅና ለሌሎች የውድ ማዕድናት ጌጣጌጦች የወጣ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
በአሜሪካ የዘንድሮ የፍቅረኞች ቀን ወጪ ቢጨምርም ዕለቱን የሚያከብሩ የአገሪቱ ፍቅረኛሞች ቁጥር ግን ባለፉት አመታት ቅናሽ ማሳየቱን የጠቆመው ዘገባው፣ ከአሜሪካውያን ጥንዶች መካከል ዘንድሮ የፍቅረኞች ቀንን ያከበሩት 51 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ብሏል፡፡

Read 8257 times