Saturday, 16 February 2019 14:42

“የመደመር” እና የፍቅር የኪነ-ጥበብ ምሽት ተካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የ“መደመር” የግጥም ውድድር አሸናፊዎች ላፕቶፕና ዘመናዊ ሞባይል ተሸለሙ

          አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከኢምር አድቨርታይዚንግ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “የመደመር” እና የፍቅር የኪነ ጥበብ ምሽት ባለፈው ሰኞ ምሽት በብሔራዊ ቴአትር ተካሄደ፡፡
በዝግጅቱ ላይ ጋዜጣው ባዘጋጀው “የመደመር” የግጥም ውድድር ከ1-3 የወጡ አሸናፊዎች ላፕቶፕና ዘመናዊ ሞባይል ስልክ ተሸልመዋል፡፡ በምሽቱ የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ገጣሚ ነቢይ መኮንን፣ ሰዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን በመደመርና በፍቅር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ግጥሞችና ወጎች አቅርበዋል፡፡
“እናቶና ህፃናት ተደምረዋል” በሚል ርዕስ የተሰናዳ ዘጋቢ ፊልምም ለእይታ ቀርቧል፡፡ የጥበብ ምሽቱ በዘመናዊ ዳንስ፣ በስታንዳፕ ኮሜዲና በክራር የታጀበ ሲሆን መድረኩን ዕውቁ ተዋናይ ፈለቀ አበበ መርቶታል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ሰዓት አክብረው ለመጡ 10 ታዳሚዎች ኢምር አድቨርታይዚንግ የእጅ ሰዓት ሸልሟቸዋል፡፡

Read 8253 times