የተደራጁ የኢንተርኔት ዘራፊዎች በህገወጥ መንገድ የሰረቋቸውን 620 ሚሊዮን ያህል የተለያዩ ድረገጾች አካውንቶች ለሽያጭ ማቅረባቸውን ፎርብስ ዘግቧል፡፡
የኢንተርኔት ዘራፊዎቹ የ16 ድረገጾችን ማለፊያ ቃል ሰብረው በመግባት 620 ሚሊዮን ያህል የተጠቃሚዎችን አካውንቶች በመዝረፍ የኢሜይል አድራሻዎችን የይለፍ ቃልና ሌሎች የግል መረጃዎች በእጃቸው ማስገባታቸውንና ለሽያጭ ማቅረባቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ አካውንቶቹን የሚገዙ ወንጀለኞች ላልተገባ ድርጊት ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ስጋት መኖሩን አመልክቷል፡፡
ባለፈው ጥር ወር ላይ 1 ቢሊዮን ያህል የኢሜይል አድራሻዎችና የይለፍ ቃሎች በኢንተርኔት መንታፊዎች መዘረፋቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ በቀናት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በ2.2 ቢሊዮን አካውንቶች ላይ ተመሳሳይ ዝርፊያ መፈጸሙንም አስታውሷል፡፡
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል