Saturday, 26 May 2012 12:46

የኢትዮጵያ ሲኒማ ባለውለታ ተሸለሙ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

ለአስር ቀናት በአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው ህያው ለትንሣኤ የፊልም ፌስቲቫል ሰሞኑን የተጠናቀቀ ሲሆን፡፡ ሚሼል አስትርዮ ፓፓን የ2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሲኒማ ባለውለታ አድርጐ መርጧቸዋል፡፡ በህያው ፕሮሞሽን የተዘጋጀውና በ2004 ዓ.ም ተሠርተው ለእይታ የበቁ 10 ፊልሞች የተሳተፉበት ፌስቲቫሉ ሲጠናቀቅ ለአገርኛ ፊልሞች ጅማሬ ከፍተኛ ውለታ አድርገዋል የተባሉት ሚሼል ፓፓታኪሲ “የ2004 የኢትዮጵያ የፊልም ባለውለታነት አዋርድ” አሸናፊ በመሆን ተሸልመዋል፡፡

“ጉማ” የተባለውን የመጀመሪያ ባለቀለም ፊልም ዳይሬክት ያደረጉት አንጋፋው የፊልም ባለሙያ በሽልማት ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “የፊልም ባለሙያዎች የአገራቸውን ወግና ባህል ያለቀቁ ሥራዎችን በመሥራት በፊልሙ ዘርፍ ሌሎች አገራት የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ እንዲችሉ ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

 

 

 

Read 934 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:48