Monday, 11 February 2019 00:00

“ሰውየው” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)

 በደራሲ አቤል እ. የተፃፈውና በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ሥራ እና እንቅስቃሴ ላይ ትኩረቱን ያደረገው “ሰውየው” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ ምንም እንኳ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ትኩረቱን ቢያደርግም “መደመር ወይስ መደናገር” በሚል ርዕስ ሥር የመደመር ፍልስፍና መፋለሶችን እና ሌሎች ጉዳዮችን በስፋት ዳስሷል፡፡
በግጥም የታጀቡ ሃሳቦች የተካተቱበት የደራሲው ሁለተኛ ስራ የሆነው መጽሐፉ በ108 ገፅ ተቀንብቦ በ99 ብር ከ99 ሳንቲም ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም “የብርሃን ናፍቆት” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም፡፡

Read 6010 times