Print this page
Sunday, 10 February 2019 00:00

የኦስካር ሽልማት ያለመድረክ መሪ እንደሚካሄድ ተነግሯል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በአለማችን ታላቁ የሲኒማው ዘርፍ ሽልማት የሆነው ኦስካር የዘንድሮው የሽልማት ስነስርዓት ባለፉት 30 አመታት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለመድረክ መሪ እንደሚካሄድ ተዘግቧል፡፡
ከአመቱ ተሸላሚዎች ባልተናነሰ የኦስካር ሽልማት ስነስርዓትን በጉጉት እንዲጠበቅ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል የመድረክ መሪዎች ንግግርና እንቅስቃሴ አንዱ እንደሆነ የዘገበው ቢቢሲ፣ የዘንድሮው ኦስካር ግን ያለመድረክ መሪ ይካሄዳል መባሉን አስታውቋል፡፡
በኤቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ የሚተላለፈውንና በመላው አለም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች እንደሚያዩት የሚጠበቀውን የ2019 የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት በመድረክ መሪነት ያጋፍረዋል ተብሎ የነበረው ኮሜዲያን ኬቪን ሃርት ከአመታት በፊት በትዊተር ዘረኝነትን የሚያንጸባርቅ መልዕክት አስተላልፏል በሚል በቅርቡ ከገጠመው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ከመድረክ መሪነቱ በፈቃደኝነት መውጣቱን አስታውቋል።
ከሳምንታት በኋላ ሎሳንጀለስ ውስጥ የሚካሄደው የዘንድሮው የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት በኦስካር ያለፉት ሶስት አስርት አመታት ታሪክ ያለመድረክ መሪ የሚከናወን የመጀመሪያው ፕሮግራም እንደሚሆን የጠቆመው ዘገባው፣ ኦስካር ያለመድረክ መሪ የተካሄደበት የመጨረሻው አመት እ.ኤ.አ 1989 እንደነበርም አስታውሷል፡፡

Read 1888 times
Administrator

Latest from Administrator