የአለማችን ቁጥር አንድ የሞባይል ስልኮች አምራች ኩባንያ ሳምሰንግ፣ በመጪው መጋቢት ወር በገበያ ላይ ያውለዋል ተብሎ የሚጠበቀው “ጋላክሲ ኤስ10” ስማርት ፎን 1ሺህ 400 የእንግሊዝ ፓውንድ የመሸጫ ዋጋ እንደተተመነለት ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
“ጋላክሲ ኤስ10” በተለያዩ 3 ቀለሞችና መጠኖች እንዲሁም በተለያየ የመሸጫ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆመው ዘገባው፤ ዝቅተኛው የመሸጫ ዋጋው 779 ፓውንድ፣ ከፍተኛው ደግሞ 1ሺህ 400 ፓውንድ ዶላር እንደሚሆን ገልጧል፡፡
በደቡብ ኮርያው የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሳምሰንግ ተመርቶ በጥቁር፣ ነጭና አረንጓዴ ቀለሞች ለገበያ ይቀርባል የተባለውና ከነባሮቹ የጋላክሲ ሞባይሎች የተለየና የተሻለ እንደሆነ የተነገረለት “ጋላክሲ ኤስ10”፤ በመጪው ወር መጨረሻ ላይ ለንደን ውስጥ በሚከናወን የምረቃ ስነስርዓት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ለእይታ ይበቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ዘገባው አመልክቷል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል