Monday, 28 January 2019 00:00

“ስንዋደድ” የኪነጥበብ ድግስ ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በምሥክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚቀርበው “ስንዋደድ” የኪነጥበብ ድግስ ከነገ በስቲያ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴያትር ይካሄዳል፡፡
በዚህ ድግስ ላይ ቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ታዋቂው ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬና ዶ/ር ሠለሞን ተሾመ ዲስኩር የሚቀርብ ሲሆን ገጣሚያኑ ኤፍሬም ስዩም፣ ትዕግስት ማሞና ምንተስኖት ማሞ ግጥሞቻቸውን፣ አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ደግሞ መነባንብ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
መሶብ የሙዚቃ ባህላዊ ባንድ በሚያጅበው በዚህ የጥበብ ድግስ ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን፤ ትኬቶቹን በጃፋር፣ በዮናስና በአይናለም መጽሐፍት መደብሮች እንዲሁም በጣይቱ ሆቴልና ካዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት ማግኘት እንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

Read 5271 times Last modified on Saturday, 26 January 2019 16:05