Saturday, 26 January 2019 13:10

አለማቀፉ የስደተኞች ተቋም በኢትዮጵያ የተፈናቃዮችን ሁኔታ በዝርዝር ይፋ አደረገ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ተቋም በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጐችን በተመለከተ ያካሄደውን ጥናት ይፋ ያደረገ ሲሆን ከተፈናቃዮች መካከል 51 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ብሏል፡፡
ተቋሙ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ማለትም ከጥር 2010 እስከ ታህሳስ 2011 ዓ.ም የተፈናቀሉ ዜጎችን አስመልክቶ በአሃዝ አስደግፎ የተለያዩ ትንታኔዎች አቅርቧል፡፡
1.773.482 ያህል ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ መፈናቀላቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ 498‚417 የሚሆኑት በአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት እንዲሁም 61‚037 ያህሉ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች መፈናቀላቸውን አመልክቷል፡፡
በተፈናቃዮች ቁጥር ኦሮሚያ ክልል ቀዳሚ ሲሆን፤ ሶማሌና ትግራይ ተከታዩን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡ አለማቀፉ የስደተኞች ተቋም ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ይፋ ባደረገው በዚህ ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች 51 በመቶ ሴቶች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ቁጥራቸው ላቅ ያለው እናቶችና ህፃናት ናቸው ብሏል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በግጭት ምክንያት 986‚458 ሰዎች ተፈናቅለው፣ በ447 የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ሲገኙ፣ 103‚440 ያህሉ በአየር ፀባይ ለውጥ የተፈናቀሉና በ44 የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ናቸው ብሏል - ሪፖርቱ። በሌሎች ምክንያቶች የተፈናቀሉት ደግሞ በ24 ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን ቁጥራቸውም 55‚950 ነው ተብሏል። በአጠቃላይ በኦሮሚያ 1‚145‚848 ሰዎች ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ እንደሆኑም ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡
በሶማሌ ክልል ደግሞ በግጭት ምክንያት 658‚582 ያህል ዜጐች ተፈናቅለው በ173 መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን 347‚649 ያህሉ ደግሞ በአየር ፀባይ ለውጥ ተፈናቅለው፣ በ216 መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ቀሪ ሪፖርቶችን ከተከታዩ ሰንጠረዥ ይመልከቱ።


    ክልል የተፈናቀሉበት ምክንያት ብዛት የተጠለሉባቸው ጣቢያዎች ብዛት
1. አዲስ አበባ በአየር ፀባይ ለውጥ
በግጭት 6583 1
በሌላ ምክንያት
አዲስ አበባ ጠ/ድምር 65.83 1
2. አፋር
በአየር ፀባይ ለውጥ 42,115 42
በግጭት 3,417 5
በሌላ ምክንያት 5,087 7
አፋር ጠ/ድምር 50,619 54
3. አማራ ክልል
በአየር ፀባይ ለውጥ 254 2
በግጭት 13,265 57
በሌላ ምክንያት
አማራ ጠ/ድምር 13,519 59
4. ድሬደዋ ጠ/ድምር
በግጭት 11,245 2
11,245 2
5. ጋምቤላ
በአየር ፀባይ ለውጥ 3,746 1
በግጭት 20,943 13
6. ሀረሪ
24,689 14
በግጭት 2,044 8
2044 8
7. በኦሮሚያ
በአየር ፀባይ ለውጥ 103,440 44
በግጭት 986,458 447
በሌላ ምክንያት 55,950 24
1,145,848 515
8. ሶማሌ
በአየር ፀባይ ለውጥ 347,694 216
በግጭት 658,582 173
በሌላ ምክንያት - -
1,006,276 389
9. ትግራይ
በአየር ፀባይ ለውጥ 1,168 5
በግጭት 70,945 144
ት/አ/ድ 72,113 149

Read 2536 times