Saturday, 12 January 2019 14:46

“ቃልና ቀለም” የሥነ ጥበብ ምሽት ሰኞ ይጀመራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በገጣሚ በላይ በቀለ ወያ እና በሄኖክ የእታገኝ ልጅ አዘጋጅነት በየወሩ የሚቀርበው “ቃልና ቀለም” ወርሃዊ የሥነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ትያትር ይጀመራል፡፡
በዚህ የጥበብ ምሽት አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ጋዜጠኛና ገጣሚ ተፈሪ ዓለሙ፣ ደራሲና ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ፣ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፣ ገጣሚ በረከት በላይነህ (አመዶ)፣ ዶ/ር ኤርሴዶ ሌንዴቦ፣ አርቲስት ሱራፌል ተካ፣ ድምፃዊ እሱ ባለው ይታየው (የሺ)፣ የሙዚቃ ሰው መአዛ ታከለ፣ ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ፣ ገጣሚ ናትናኤል ጌቱና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም የሚገኙበት ሲሆን፤ መድረክ መሪው አርቲስት ሽመልስ በቀለ ነው ተብሏል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ትኬቶቹ በጃፋር መጽሐፍ መደብር፣ በዮናስ መጽሐፍ መደብር እና በእለቱ ብሔራዊ ትያትር በር ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

Read 7643 times