አገልግሎቱ በአይነቱ በአገሪቱ የመጀመሪያው ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ከውጭ አገራት የሚላክላቸውን ገንዘብ በሲቢኢ ብር አማካይነት በቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው እንዲደርሳቸው የሚያደርግና በአይነቱ በአገሪቱ የመጀመሪያው የሆነ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ወርልድሪሚት ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር በመተባበር ህብረተሰቡ በአገሪቱ በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነው የዚህ ምቹና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪውን ያቀረበው ባንኩ፣ የአገልግሎቱን መጀመር የሚያበስር ልዩ ስነስርኣት በመጪው ማክሰኞ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የወርልድሪሚት የምስራቅና ማዕከላዊ አፍሪካ ቀጠና ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች ተወካዮች በሚገኙበት እንደሚከናወንም ለአዲስ አድማስ በላከው መረጃ አክሎ ገልጧል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየጊዜው ዘመኑ ያፈራቸውን የባንክ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ደንበኞቹ ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ በሆነ መንገድ የባንክ አገልግሎትን እንዲያገኙ ሲያደርግ እንደቆየም አስታውሷል፡፡
Saturday, 12 January 2019 14:12
ንግድ ባንክ ከውጭ የሚላክን ገንዘብ በቀጥታ በሞባይል መቀበል የሚያስችል አገልግሎት ጀመረ
Written by አለማየሁ አንበሴ
Published in
ዜና