Monday, 07 January 2019 00:00

“አብራክ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር በሆኑት ደራሲ ሙሉጌታ አረጋይ የተደረሰው “አብራክ” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡
ምሁሩ የጀርመን የራዲዮ ድምፅን ጨምሮ በአገር ውስጥና በውጭ ባሉ የመገናኛ ብዙኃን ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ፣ ሲከራከሩና ሲሟገቱ የቆዩ ሲሆን ይህንኑ ተሞክሯቸውን በልቦለድ መልክ እንደጻፉት በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ጠቅሰዋል፡፡
መፅሐፉ ማህበራዊና አገራዊ ሃሳቦችን የተወከሉ መቼቾችና ገፀ ባህሪያት የሚያንፀባርቅ ነው ተብሏል።
በ453 ገጾች የተቀነበበው “አብራክ” ፤በ220 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “ዲቪ ሎተሪ” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡  

Read 2624 times