Sunday, 06 January 2019 00:00

የብሩህ ዓለምነህ ‹‹ፍልስፍና ፫›› ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተለያዩ ፍልስፍናዊ ፅሁፎችን በማስነበብ የሚታወቀው ደራሲ ብሩህ ዓለምነህ፤ ‹‹ፍልስፍና ፫›› የተሰኘ አራተኛ መፅሐፉን ለገበያ አቀረበ፡፡ መጽሐፉ፤ ‹‹የባህልና ትውፊት ተቋም የሆነችው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ የህዳሴና የዘመናዊነት ፕሮጀክት ውስጥ በባለቤትነት የማትሳተፍ ከሆነ ወደፊት የሚገጥማትን ፈተና፣ እንዲሁም ሠሞነ ሕማማት እንዴት የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ምንጭ እንደሆነ›› ያብራራል፡፡ በተጨማሪም፣ በቅኔና በፍልስፍና መካከል ያለውን ፉክክር ይተነትናል፡፡
 በ148 ገጾች የተሰናዳው መጽሐፉ፤በ71 ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ ነው፡፡ ደራሲው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ሲሆን ከዚህ ቀደም ‹‹ፍልስፍና ፩››፣ ‹‹ፍልስፍና ፪›› እና ‹‹የኢትዮጵያ ፍልስፍና›› የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባብያን ማድረሱ  ይታወሳል፡፡

Read 1270 times