Sunday, 06 January 2019 00:00

“ጋሻው” ታሪካዊ ልብ ወለድ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)


    በደራሲ ተክልዬ በቀለ (ዶ/ር) የተጻፈው “ጋሻው” ታሪካዊ ልብ ወለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ። መቼቱን ኢትዮጵያና ጀርመን ሀምቡርግ ያደረገው መጽሐፉ፤ያለፈ ታሪክን ከአሁኑ የማገናኘት ግብ ያለው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ “ያለፈ ታሪክ ለአሁኑ መሰረት ነው” በሚል መርህ የተዘጋጀው ታሪካዊ ልብ ወለዱ፤በተለይ በአሁኑ ወቅት በዘረኝነት ጦስ አገሪቱ ላይ እየደረሰ ያለውን ኪሳራና የወደፊት ስጋት በግጥም እያዋዛ ይነቅፋል ተብሏል፡፡  በ226 ገጾች የተመጠነው መጽሐፉ፤በ125 ብር እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 862 times