የሊፋን ልዩ አምባሳደር በመሆን አዲሱዋን “ሊፋን X-60” መሸለሙን በተመለከተ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ “ለሽልማቱ ያበቃኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫፍ ጫፍ የሰጠኝ ፍቅር ነው ለተደራራቢ ድሎች ያበቃኝ” መላው ህዝብ ይመስገንልኝ” ብሏል-ኮሜንታተር መሰለ፡፡ሊፋን ሞተርስ “ሪካርዶ” ከተባለው የብሪቲሽ ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር በመተባበር ቪቪ ቲ አይ የተባለ የስፖርት መኪና ሞተር ለአዲሱዋ አውቶሞቢል እንደተገጠመላት የገለፁት የኩባንያው ሃላፊ “ሞተሩ መኪናዋ በአነስተኛ ነዳጅ ከፍተኛ ጉልበት እንዲኖራት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ለኩባንያው በቀረበ ትዕዛዝ መሰረት” በመጪው ሁለት ወር ውስጥ 40 ሊፋን መኪናዎች ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ ተገልፅዋል፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ከ3ሺ በላይ የሊፋን ምርት የሆኑ መኪኖች መሸጣቸውን የገለፁት የኩባንያው ኃላፊ” መኪኖቹ በትዕዛዝ ቶሎ ግዢያቸው ሊፈፀም መቻሉ ተፈላጊ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡