Saturday, 22 December 2018 08:08

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች ረብሻ ፈጠሩ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት “ይቅር ተደርጐልን መፈታት አለብን” የሚሉ እስረኞች ከትናንት በስቲያ ከሐሙስ ጀምሮ ረብሻ በማስነሳት የእርስ በርስ ግጭት መፈጠሩ ታውቋል፡፡
በማረሚያ ቤቱ ዞን ሁለት በተባለው ክፍል ከአዲስ አበባና ከፌደራል የፍትህ አካላት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች የታራሚዎችን አያያዝ በተመለከተ በአካል ተገኝተው ለመታዘብ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ረብሻው መቀስቀሱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ታራሚዎቹ በዋናነት “የይቅርታ ማመልከቻ አስገብተን፣ እንዴት እስካሁን ሳንፈታ ቆየን፤ ልንፈታ ይገባል” በሚል ተቃውሞ መጀመራቸውን የገለፁት ምንጮች፤ ይኸም ወደ እርስ በእርስ ግጭት አምርቶ በድንጋይና በተለያዩ ቁሳቁሶች በመታገዝ፤ በርካቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል፡፡
ረብሻው መፈጠሩን ለአዲስ አድማስ ያረጋገጡት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው፤ ግጭቱና ረብሻው ብዙም ሳይስፋፋ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
ታራሚዎቹ ዞን ሁለትን ከዞን ሶስት የሚለየውን አጥር በማፍረስ ሁለቱን ዞኖች የቀላቀሉ ሲሆን ወደ ሴቶች ማረፊያ ለመግባትም ሙከራ ማድረጋቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡




Read 8848 times