ከተቋቋመ 10 ዓመት ያስቆጠረው ማራቶን ኢንጂነሪንግ፤ የሂውንዳይ መኪኖች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሰሞኑን አስመርቋል፡፡ በሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረው የፋብሪካ ግንባታው፤ በአመት ከ8 ወር ውስጥ ተጠናቆ መኪኖችን ማምረት እንደጀመረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ የኤሌትሪክ መኪና ለማምረት ማቀዱን፣የኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡
የሂውንዳይ መኪኖችን እያስመጣ ሲሸጥ የቆየው ማራቶን ኢንጂነሪንግ፤አሁን በአገር ውስጥ መገጣጠም በመጀመሩ ዋጋው ከ15-18 በመቶ እንደሚቀንስ ታውቋል፡፡ ፋብሪካው በቀን 36፣ በዓመት 10ሺ አውቶሞቢሎችን እንደሚያመርት የማራቶን ኢንጂነሪንግ ሊቀመንበር አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴና ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መልካሙ አሰፋ፣ከትላንት በስቲያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡ በአፍሪካ ሂውንዳይ መኪኖችን የመገጣጠም ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ሦስት አገራት ብቻ ናቸው ያለው አትሌት ኃይሌ፤ ይሄ የሚያሳየው ይችላሉ ብለው በእኛ ላይ እምነት ማሳደራቸውን ስለሆነ
ትልቅ ነገር ነው ብሏል፡፡
Published in
ባህል
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል