Sunday, 16 December 2018 00:00

ፎርብስ በአመቱ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ የዓለማችን ደራሲያንን ይፋ አደረገ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  ታዋቂው ፎርብስ መጽሄት በፈረንጆች አመት 2018 ከፍተኛ ገቢ ያገኙ የዓለማችን ምርጥ ደራሲያንን ይፋ ያደረገ ሲሆን ዘ ፕሬዚደንት ኢዝ ሚሲንግ የተሰኘ ተወዳጅ ስራቸውን ጨምሮ ከመጽሃፍቶቻቸው ሽያጭ ባገኙት 86 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ቀዳሚነቱን ይዘዋል፡፡
ደራሲው በፎርብስ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ የአለማችን ደራሲያን ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ የዘንድሮው ለአስረኛ ጊዜ ሲሆን፣ የመጀመሪያ መጽሃፋቸውን እንዲያሳትሙላቸው የጠየቋቸው 31 ያህል ደራሲያን መጽሃፉን አይረባም በሚል እንደመለሱባቸውም ፎርብስ አስታውሷል፡፡
በፎርብስ የአለማችን ባለከፍተኛ ገቢ ዝርዝር ውስጥ የሁለተኛነት ደረጃን የያዘቺው ታዋቂዋ እንግሊዛዊት ደራሲ ጄ ኬ ሮውሊንግ ስትሆን፣ ደራሲዋ በአመቱ ከመጽሃፍቶቿ ሽያጭና ተያያዥ ገቢዎች በድምሩ 54 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገቢ ማግኘቷ ተነግሯል፡፡
በአመቱ 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኙትና ዘ ኪንግ ኦፍ ሆረር የተሰኘው ድንቅ መጽሃፋቸው በገፍ የተሸጠላቸው ታዋቂው ደራሲ ስቴፈን ኪንግ በዘንድሮው የፎርብስ ዝርዝር ውስጥ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ ጆን ግሪሻም በ21 ሚሊዮን ዶላር፣ ጄፍ ኬኒና ዳን ብራውን በ18.5 ሚሊዮን ዶላር አራተኛና አምስተኛ ደረጃን ሲይዙ፣ ዳን ብራውን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዙሪያ የሚያጠነጥነው ፋየር ኤንድ ፊዩሪ የተሰኘው መጽሃፋቸው በአለማቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ አድርጓቸው የከረመው አሜሪካዊው ደራሲ ሚካኤል ውልፍ፣ መጽሃፉን በወረቀት ህትመት ብቻ 1.7 ሚሊዮን ቅጂ መሸጣቸውንና በድምሩ 13 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት በስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በአለማችን በአመቱ ከፍተኛ ገቢ ያገኙት 11 ምርጥ ደራሲያን በድምሩ 24.5 ሚሊዮን የመጽሃፍት ቅጂዎችን በመሸጥ 283 ዶላር ያህል ገቢ ማግኘታቸውንም ፎርብስ መጽሄት ባለፈው ረቡዕ ይፋ ባደረገው መረጃ አስታውቋል፡፡

Read 2750 times