Print this page
Saturday, 15 December 2018 14:52

ከክብደት በታች የሚወለዱ ልጆች ምክንያትና መፍትሔው

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 ከክብደት በታች መወለድ ማለት አንድ ህጻን ሲወለድ ሊኖረው ከሚገባው ክብደት በታች ሲኖረው ማለት ነው፡፡ አንድ ህጻን በሚወለድበት ወቅት ክብደቱ 2.500/ግራም ሲደርስ ትክክል ነው ይባላል፡፡
አዲስ ከሚወለዱና እድሜያቸው ከአንድ ወር በታች ከሆኑ ሕጻናት 3/4ኛ የሚሆኑት የሚሞቱት በተወለዱ በመጀመሪያው ሳምንት ነው፡፡
ከአንድ አራተኛው በላይ የሚሆኑት ደግሞ በመጀመሪያው 24/ሰአት ጊዜ ውስጥ ይሞታሉ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ 40% የሚሆኑት ጨቅላ ሕጻናት የሚሞቱት እድሜያቸው ከ5/አመት በታች ሳለ ነው፡፡
የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በአንድ አመት ለአራት ጊዜ በሚያወጣው ጆርናል Volume 10 No. 2 April, 2018 ላይ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች በሆኑት በዶ/ር ትዝታ አብርሀምና በዶ/ር አብዱልፈታህ አብዶሽ የወጣው ጥናት ከክብደት በታች ስለሚወለዱ ጨቅላዎች ጠቃሚ ሀሳቦችን ያስነብባል። ባለሙያዎቹ ያወጡት ጥናት እንደሚያመለክተው በእድሜ ከ0-7/ቀናት የሆናቸውና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በአንድ አመት ውስጥ በተወለዱ ጨቅላዎች ላይ ለአንድ አመት በተሰራው ስራ ጨቅላዎቹ በምን ምክንያት ከክብደት በታች ሆነው እንደተወ ለዱና በምን አይነት ክትትል ወደ ደህና ሕይወት እንደተቀላቀሉ ያሳያል፡፡
ክብደታቸው እጅግ አናሳ ነው የሚባሉት አዲስ ተወላጆች ወይንም እድሜያቸው ከአንድ ወር በታች የሆኑ ሲሆኑ ክብደታቸውም በግምት ከ1000-1499/ግራም ወይንም 1.30/ኪሎ የሆናቸው ናቸው፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ  በህይወት ከተወ ለዱት ልጆች ውስጥ  4-7/% የሚሆኑት ከክብደት በታች ሆነው የተወለዱ ሲሆን ይህም ምናልባት ለከፋ የጤና ችግር ወይንም ለሞት ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡
ለጥናቱ በምክንያትነት የተቀመጠውም በሆስፒታሉ ከሚወለዱ ጨቅላዎች ምን ያህሉ ከክብደት በታች ሆነው እንደሚወለዱ ለማወቅና ምን አገልግሎት ቢሰጥ ሕይወታቸውን ለመ ቀጠል ያስችላቸዋል የሚለውን እና አገልግሎቱንም በተገቢው ለማዳረስ እንዲሁም የጨቅላዎቹ ሕይወት በጥሩ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል አመላካች ነገሮችን ለመጠቆም ነው፡፡
ጥናቱም ለአንድ አመት ያህል ማለትም ከጃንዋሪ 1-ዲሴምበር 31/2016 ያሉትን በጣም ከክብደት በታች የተወለዱ 161/ጨቅላዎችን ያካተተ ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሰባት ቀናት በሕይወት የመኖራቸው ወይንም ከሆስፒታሉ እንዲወጡ መደረጉ አለዚያም በሕይወት መኖር አለመኖራቸው በሐኪሞቻቸው የሚሰጠውን ማረጋገጫም ጥናቱ አካቶአል፡፡
ጥናቱ እንደሚያረጋግጠው የመወለጃ ጊዜያቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ልጆች በሕክምናው ዘርፍ አንዱ አስቸጋሪ ሁኔታ ነው። እንደ አስቸጋሪ የሚታይበት ምክንያትም የሚወለደውን ሕጻን ለማትረፍ ወይንም ሙሉ ጤንነቱ የተሟላ እንዲሆን እንዲሁም አካሉ እንዳይጎድል ለማድረግ የሚሞከረውን እንዳይሳካ ሊያደርግ ስለሚችል ነው፡፡ አዲስ የተወለዱ ሕጻናት በክ ብደታቸው ከ1000-1499/ግራም የሚሆኑበት አንዱ ምክንያትም የመወለጃ ጊዜያቸውን ሳይጨ ርሱ ስለሚወለዱ ነው፡፡   
ከክብደት በታች ሆነው በሚወለዱ አዲስ ሕጻናት ላይ የሚከሰተው የሞት አደጋ በጤናማ ክብደት ከሚወለዱት 30/ጊዜ የበለጠ ነው፡፡ እነዚህ ህጻናት በሆስፒታል አልጋ ይዘው ለረጅም ቀናት የሚቆዩ ሲሆን በሕክምናው የሚደረግላቸው አገልግሎትም በበጀት ሲሰላ ከፍተኛ ነው፡፡ ካለቀናቸው ከክብደት በታች ሆነው በሚወለዱ ልጆች ሕክምና ምክንያት የሚወጣውን በጀት በአሜሪካ ያሰላ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በአመት 26/ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል፡፡
በእርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ላለፉት አስርት አመታት ገና የተወለዱ ሕጻናት ሞት በተለይም ባደጉት ሀገራት በስፋት የቀነሰ መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ የዚህ ምክንያቱም በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ ችግር የገጠማቸውን እናቶች እንዲሁም ህጻናቱ ከተወለዱ በሁዋላ ያለውን የጤና አገልግሎት በተሻሻለ መንገድ መስጠት በመቻላቸው ነው፡፡ በአፍሪካ ካለጊዜያ ቸው እና ከክብደት በታች ሆነው አዲስ የተወለዱ ሕጻናትን ሕይወት የመታደግ ነገር እስከአሁን ብዙም አስደንጋጭ ነገር አይታይም እንደጥናቱ ፡፡
በኢትዮጵያ በተደረገ የማህበረሰብ እና የጤና ዳሰሳ እንደተገኘው እውነታ ከ1000/ በሕይወት ከሚወለዱ ሕጻናት ውስጥ 29/የሚሆኑት ጨቅላዎች ይሞታሉ፡፡ ከክብደት በታች ስለሚወለዱ ሕጻናት ሁኔታ በስፋት የሚዘገበው በአደጉት ሀገራት ሲሆን በመልማት ላይ ባሉ ሀገራት ግን መረጃው ብዙም አይደለም፡፡ ስለዚህም ለማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ከክብደት በታች አለቀናቸው ስለሚወለዱ ጨቅላዎች ደህንነት ወይንም በሕይወት የመቀጠል ሁኔታ ለመገመት እንደሚያ ስቸግር እሙን ነው፡፡ ስለሆነም ገና የተወለዱ ጨቅላዎችን ሕይወት ለማስቀጠል እንዲቻል የተለያዩ ጥናቶች ቢሰሩ ጥሩ እገዛ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይህ ጥናት ያሳያል፡፡   
ጥናቱ በተደረገበት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካ ኮሌጅ በውጭው አቆጣጠር ከጃንዋሪ 1-ዲሴምበር 31/2016 ድረስ ከክብደት በታች የተወለዱ ጨቅላዎች ሁኔታ ተካቶአል፡፡ በሕይወት የተወለዱት ጨቅላዎች ክብደት ከ1000-1499/የሚደርስ ሲሆን የተፈጥሮ ችግር ያለባቸውን እና ሞተው የተወለዱትን ግን  ጥናቱ አልተመለከተም፡፡
በሆስፒታሉ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከነበረው 9.531/ የማዋለድ ስራ 9.883/ልጆች የተወለዱ ሲሆን ከእነዚህ ልጆች መካከል ከክብደት በታች ሆነው የተወለዱት 264(2.7%) ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 193/የሚሆኑት በሕይወት የተወለዱ ናቸው። የተቀሩት በሕይወት የሌሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለጥናቱ የተያዙት 161/ከክብደት በታች የሆኑ ጨቅላዎች በጥናቱ የተካተቱ ቢሆንም 32/የሚሆኑት ግን በነበረባቸው ተፈጥሮአዊ ችግር የተነሳ አልተተኮ ረባቸውም፡፡
ጨቅላዎች ከክብደት በታች ሆነው ለምን ይወለዳሉ ሲባል የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንድ ልጅ የመወለጃ እድሜው ከመድረሱ በፊት ሲወለድ ብዙ ጊዜ ከክብደት በታች መሆኑ የሚያጋጥም ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ተጠቃሽ የሚሆኑት፤ ከክብደት በታች የሆነ ልጅን መውለድ በዘር የሚተላለፍ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት እንደተገለጸው ብዙ ጊዜ አፍሮ አሜሪካን የሚባሉ ዘሮች ከነጮቹ ይበልጥ ከክብደት በታች የሆነ ልጅ እንደሚወልዱ Standard children health  የተሰኘው ድረገጽ ለንባብ ብሎታል፡፡
ከላይ በተገለጸው ድረ ገጽ በመቀጠል የተመለከተው….
እድሜያቸው ከ15/አመት በታች የሆኑ ሴት ልጆች የሚኖራቸው እርግዝና ጽንሱ ካለጊዜው የመወለድና ከክብደት በታች መሆንን ያጋጥማል፡፡
ከአንድ በላይ ማርገዝ ሌላው ምክንያት ነው፡፡ መንትያም ይሁን ሌላ መጠን በአንድ ጊዜ መውለድ ሌላው ከክብደት በታች ልጅ ለመውለድ ምክንያት ነው፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ መንትያዎችና ሌሎችም ክብደታቸው ከመጠን በታች ሆኖ መወለዳቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የእናቶች ጤንነት አለመሟላት ሌላው ከክብደት በታች ልጅ እንዲወለድ ምክንያት ነው፡፡ በተለይም የተለያዩ መድሀኒቶችን ፤አልኮሆል፤እና ሲጋራ ማጤስ የሚያዘወትሩ እናቶች ጽንስ ዝቅተኛ ክብደት ይዞ ይወለዳል፡፡
በአኑዋኑዋርም ዝቅተኛ በሆነ ደረጃ ያሉ እናቶች የተመጣጠነ ምግብ ስለማያገኙ እና በእርግዝናቸው ወቅት ተገቢውን እንክብካቤ ስለማያገኙ ጽንሱ ሲወለድ ከክብደት በታች ሊሆን ይችላል፡፡
የደም ግፊታቸው ያልተስተካከለ እናቶች በእርግዝና ወቅት ጽንሱን ከክብደት በታች የመወለድ ችግር እንደሚገጥማቸው ተስተውሎአል፡፡ ብዙውን ጊዜም በደም ግፊቱ ምክንያት እናትየው እንዳትጎዳ ሲባልም ጽንሱ ከመወለጃ ጊዜው አስቀድሞ እንዲወለድ ስለሚደረግ ከክብደት በታች የመሆን አጋጣሚው ከፍ ያለ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በተደረገው የአንድ አመት ጥናት ከክብደት በታች የተወለዱ ጨቅላዎች 2.7% ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 77.0% የሚሆኑት በመጀመሪያው ሰባት ቀን በሁሉም መስክ ጤንነታቸው ተመርምሮ አገግመዋል፡፡ ቀደም ሲል የተሰሩ ጥናቶች ሲነጻጸሩ ችግሩ እየተቀረፈ በመሄድ ላይ መሆኑን ያሳያል። ለም ሳሌም በጂማ ሆስፒታል ከጃንዋሪ 2012-ዲሴምበር 2012/ የነበረው 56% እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከጁላይ 2011-ጁን 2012/ 60.8% ያህል ከክብደት በታች የተወለዱ ጨቅ ላዎች ተመዝግበው ነበር፡፡
እንደመፍትሔ ከሚወሰዱት መካከል ዋነኛው በእርግዝና ወቅት ያላሰለሰ ክትትል ማድረግ ነው፡፡ ይህ ክትትል በጽንሱም ሆነ በእናትየው ላይ ምንም አይነት ችግር ከመከሰቱ በፊት እርምጃ ለመውሰድ ስለሚያስችል ህብረተሰቡ ችላ ሊለው አይገባም፡፡  

Read 3494 times