Saturday, 19 May 2012 11:43

የአዳም ረታ “ህማማትና በገና” እየተሸጠ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

ለየት ባለ የአፃፃፍ ስልቱ የሚታወቀው ደራሲ አዳም ረታ ሰባተኛ የልቦለድ መጽሐፉን ሰሞኑን ለንባብ ያበቃ ሲሆን፤ በቅርቡ ሌላ የረዥም ልብወለድ መፅሐፍ እንደሚያሳትም ታውቋል፡፡ “ሕማማትና በገና” የተሰኘው አዲሱ የአጭር ልብወለዶች መድበል አስራ ሦስት ታሪኮችን አካትቷል፡፡ በ240 ገፆች የተቀነበበው መድበሉ፤ በ39 ብር እየተሸጠ ሲሆን፤ አንዳንድ አዟሪዎች ዋጋውን በመሰረዝ ጭማሪ እንደሚያደርጉ የጠቆመው አሳታሚው፤ አንባቢያን ከ39 ብር በላይ እንዳይገዙ አሳስቧል፡፡

ደራሲው “የስንብት ቀለማት” የተሰኘ ረዥም ልብወለድ በቅርቡ ለህትመት እንደሚያበቃ አስታውቋል፡፡ አዳም ረታ ከዚህ ቀደም “ማህሌት”፣ “ግራጫ ቃጭሎች”፣ “አለንጋና ምስር”፣ “እቴሜቴ ሎሚ ሽታ”፣ “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” እና “ይወስዳል መንገድ፣ ያመጣል መንገድ” የተሰኙ ልብወለድ መጽሐፍትን ለአንባቢ ማድረሱ ይታወቃል፡፡

 

 

 

Read 1530 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 12:52