Saturday, 19 May 2012 11:42

“ወይዘሪት ኢትዮጵያ” የቁንጅና ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

ባለፉት አመታት ከሽልማት ጋር በተያያዘ ውዝግብ ታጅቦ ሲካሄድ የነበረው “ወይዘሪት ኢትዮጵያ” የቁንጅና ውድድር ዛሬ ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያን ቪሌጅ ያዘጋጀው የቁንጅና ውድድር ዛሬ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በአዲሱ የራዲሰን ብሉ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን ከሐረር፣ ከአዲስ አበባ፣ ከኦሮሚያ፣ ከጋምቤላና ከትግራይ ክልሎች የመጡ ቆነጃጅት ይሳተፉበታል፡፡ የባህልና ቱሪዝምን ማስተዋወቅ የሚጠበቅባትን ቆንጆ ለመምረጥ ከደምግባት በተጨማሪ ባህልና ቱሪዝምን የተመለከቱ ጥያቄዎች ለተወዳዳሪዎች እንደሚቀርብላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ውድድሩ ለሦስተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በሁለተኛው ውድድር ከመኪና ሽልማት ጋር በተያያዘ ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አዘጋጆቹ አሁን ውዝግብ የለም፡፡ ሽልማት በዕለቱ ይሰጣል ብለዋል፡፡ የሽልማቱን አይነት በተመለከተ ተጠይቀውም “ከወትሮው ለየት ይላል፤ ቆነጃጅት ግን ሽልማቱን ታሳቢ አድርገው መወዳደር የለባቸውም” ብለዋል፡፡ ዛሬ ለሚካሄደው ውድድር ሽልማት እስካለፈው ማክሰኞ ድረስ ስፖንሰር የሚያደርግ ድርጅት አለመገኘቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

 

 

 

Read 1584 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 14:20