Monday, 10 December 2018 00:00

ጅቡቲ በወደብ አገልግሎት ታሪፍ ላይ ቅናሽ ልታደርግ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 ኢትዮጵያ ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ተጨማሪ ወደቦችን ለመጠቀም የምታደርገውን እንቅስቃሴ በበጎ መልኩ እንመለከተዋለን ያለው የጅቡቲ መንግስት፤ በኢትዮጵያ በኩል በወደብ መጠቀሚያ ታሪፍ ላይ ቅናሽ እንዲደረግ የቀረበውን ጥያቄ መቀበሉንና በወደቡ የታሪፍ መጠን ላይም ማሻሻያ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ እርቅ መፈፀማቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ወደቦች ማማተሯ አያስከፋንም ያሉት የጅቡቲ የወደብ ኃላፊ ዋሂብ ዳሂር፤ 100 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሃገር ተጨማሪ ወደብ ማፈላለጓ ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡
95 በመቶ የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ሸቀጥ በጅቡቲ ወደብ እንደሚስተናገድ ያወሱት ኃላፊው፤ ሸክሙ መቃለሉ የወደቡን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ ያግዘናል እንጂ አይጎዳንም ብለዋል፡፡
ተጨማሪ ወደቦችን በመገንባት እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን የውጪ ንግድ እንቅስቃሴ ለማስተናገድ ሃገራቸው መዘጋጀቷንም ዋሂብ ዳሂር አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከጅቡቲ ወደብ በተጨማሪ የሶማሊያ በርበራ ወደብንና የሱዳን ወደብን ለመጠቀም ከየሃገራቱ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡


Read 7377 times