Print this page
Saturday, 19 May 2012 11:31

“ዕንባና ሳቅ” ከ21 ዓመት በኋላ ታተመ “የዳግማዊ ገፆች” ለንባብ በቃ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

የደራሲ ገበየሁ አየለ ልቦለድ ሥራ የሆነው “ዕንባና ሳቅ” ልቦለድ መጽሐፍ ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ ሦስት ሺህ ቅጂ የታተመው መጽሐፍ 221 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው 39 ብር ነው፡፡ ይኸው መጽሐፍ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሬዲዮ ፋና ይባል በነበረው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሲተረክ ከፍተኛ አድማጭ ነበረው ያሉት የፋና ኤፍ ኤም 98.1 ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዘካሪያስ ብርሃኑ፤ ትረካው እጅግ ከፍተኛ የሕዝብ አስተያየት እንደነበረውና አድማጮች መጽሐፉን የት ማግኘት እንደሚችሉ በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን አስታውሰዋል፡፡ በአሁኑ ሕትመት የመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን አስተያየቶች ላይ ዋና አዘጋጁ ከፃፏቸው መካከልም “የኮቴው ዱካ ጠፍቶባቸው አመለጠን ላሉ አንባብያን ይህ ዜና ታላቅ የምስራች እንደሚሆን አምናለሁ” ብለዋል፡፡ “ጣምራ ጦር” በሚለው መጽሐፉ ይበልጥ የሚታወቀው ደራሲ ገበየሁ አየለ አምና ኮድ ኢትዮጵያ አዘጋጅቶት በነበረው የእንግሊዝኛ ልቦለድ ውድድር  “ESCAPE” የተሰኘ መጽሐፉ ሁለተኛ በመውጣት የ103 ሺህ ብር ተሸላሚ እንዳደረገው ይታወሳል፡፡

በሌላም በኩል በአሸናፊ ለገሠ የተፃፈው “የዳግማዊ ገፆች” የተሰኘ ረዥም ልቦለድ መጽሐፍ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ለንባብ በቃ፡፡ 224 ገፆች ያሉት መጽሐፍ ዋጋ 35 ብር ነው፡፡ በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ በሰጡት አስተያየት፤ ደራሲውን በጭብጡ መምህራንን በማግዘፍ ሀዲስ አለማየሁን፣ በዓሉ ግርማንና የሺጥላ ኮከብን ተቀላቅሏል፡፡ ይህንንም ፍረዱኝ በማለት አንባቢዎች መጽሐፉን እንዲያነቡ ጋብዟል፡፡

 

 

Read 1499 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:40