Saturday, 19 May 2012 11:30

ንባብን ያበረታቱ ግለሰቦችና ተቋማት ተሸለሙ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር በአገሪቱ የንባብ ባህል እንዲስፋፋና እንዲዳብር የበረታቱ ግለሰቦችና ተቋማትን ሸለመ፡፡የዛሬ ሳምንት በጣይቱ ሆቴል በተደረገ የምሳ ግብዣ ማህበሩ ለተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡ከተሸለሙት መካከል ለአራት አስርት ዓመታት መጽሐፍ አዙሮ በመሸጥ የሚተዳደሩ ግለሰብ ይገኙበታል፡፡ የደራስያን ማህበሩ አቶ ይልማ በረካና አቶ ተስፋዬ አዳል የተባሉ ግለሰቦችን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስን እና አስቴር ነጋ አሳታሚን ሸልሟል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ቁምነገር መጽሔት፣ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ሰንደቅ ጋዜጣ እና ሌሎችም ተሸላሚ ሲሆኑ ከመፃሕፍት አከፋፋዮች አቶ ተክሌ ገብሬ፣ አቶ አይናለም መዋ እና አቶ ጃዕፋር ሽፋ ተሸልመዋል፡፡

 

 

Read 1061 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:40