Saturday, 24 November 2018 13:07

የዓለማየሁ ገላጋይ “ታለ (በእውነት ሥም)” ዛሬ በገበያ ላይ ይውላል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)


የንጋፋው ደራሲ፣ ሀያሲና ጋዜጠኛ ዓለማየሁ ገላጋይ 12ኛ ሥራ የሆነው “ታለ (በዕውነት ሥም)” የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መፅሐፍ ዛሬ በገበያ ላይ ይውላል፡፡ የታሪኩ ዋና አካል እውነትና ውሸት ተደባልቆ ህይወቱን የሚበጠብጠው አንድ ገፀባህርይ ላይ የተመሰረተ ሲሆን አንዳንድ እውነት ውሸት እየመሰለ፣ አንዳንድ ውሸት እውነት እየመሰለ በኋላ ውሸትነቱ ወይም እውነትነቱ የሚያመጣውን ስነ - ልቦናዊ ጫና እንዲሁም በተለይም እውነትና ውሸት የተደበላለቀበትን ይህን ዘመን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ብሏል ደራሲው፣  በ220 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም የ “ብርሃን ፈለጎች”፣ “ቅበላ”፣ “ስብሃት ገ/እግዚአብሔር - ህይወትና ክህሎት፣ “ኢህአዴግን እከስሳለሁ”፣ “ኩርቢት”፣ “ወሪሳ”፣ “አጥቢያ”፣ “በፍቅር ስም”፣ “የፍልስፍና አፅፍ”፣ “መለያየት ሞት ነው” የተሰኙ መፃሕፍትን ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ሲሆን 27 ፀሐፍት፣ ደራሲያንና ገጣሚያን የተሳተፉበት “መልክዓ-ስብሃት” የተሰኘ መፅሐፍም አሰናድቶም ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 7161 times