Saturday, 19 May 2012 11:25

የህፃናት የካርቱን ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ከአፀደ ህፃናት እስከ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች የስዕልና የካርቱን ሥራ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት የህፃናት የካርቱን ፌስቲቫል ዛሬ ይከፈታል፡፡በአዲሱ ኤሊያና ሞል ዛሬ በማካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ከአፀደ ህፃናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ የህፃናት የካርቱን ስዕል ሥራዎችና ኢሉስትሬሽን ለእይታ ይበቃሉ፡፡ የፕሮግራሙ አላማ ህፃናቱ ተሰጥኦቸውን እንዲያዳብሩ ለማበረታታትና ከሌሎች ተማሪዎችና ባለሙያዎች ልምድና ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ መሆኑን የገለፀችው የአዲስ አፍሪካ ኤቨንትስ ማኔጅመንት ፒ.ኤል.ሲ የፕሮግራም እቅድና አገልግሎት ዋና አስተባባሪ ወ/ሪት መቅደላዊት ዳግማዊ ፕሮግራሙ በየዓመቱ ቀጣይ እንዲሆን ለማድረግና ተማሪዎቹን እያወዳደሩ ለመሸለም እቅድ እንዳላቸው ተናግራለች፡፡

ፕሮግራሙ በአዲስ አፍሪካ አቨንትስ ማኔጅመንት እና በIBI.S ኢንተርናሽናል የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩቨርሲቲ የተውጣጡ ምሁራንና በርካታ ታዋቂ ሰዎች በፕሮግራሙ ላይ እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡አዲስ አፍሪካ ኤቨንትስ ማኔጅመንት ከወራት በፊት በግዮን ሆቴል ተካሂዶ የነበረውን የሠርግ ኤግዚቢሽን ያዘጋጀ መሆኑ ይታወሳል፡፡

 

 

Read 949 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:28