Print this page
Saturday, 19 May 2012 11:25

“መፍቻው” እና ሌሎች አጫጭር ልቦለዶች በስጦታ ይበረከታል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(6 votes)

ከ12-18 ዓመት ያሉ ታዳጊዎች ላይ እና በሥነ ምግባር ያተኮረው “መፍቻው” እና ሌሎች  አጫጭር ልቦለዶች መፅሐፍ 2000 ቅጂ በነፃ ሊታደል መሆኑን የዜማ ብዕር የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር አስታወቀ፡፡ የደራሲ የዝና ወርቁ የብዕር ትሩፋት የሆነው መፅሐፍ በነፃ የሚታደለው ነገ በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ትንሿ አዳራሽ ነው፡፡ መፃህፍቱ የሚሰጡት የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ለሚያካሂዱ ሬዲዮ ጣቢያዎችና ለ30 ትምህርት ቤቶች ይሰጣሉ፡፡ ከሚሰጣቸው ሬዲዮ ጣቢያዎች መካከል በአፍኤም አዲስ 97.1 የሚተላለፈው “ብራና” የሬዲዮ ፕሮግራም እና ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ይገኙበታል፡፡መፅሐፉን ከገዙት ድርጅት መካከል ሕብረት ባንክ፣ ብሔራዊ ሎተሪ፣ ሕብረት ኢንሹራንስ፣ አልታድ፣ ኮሰሞ እና የአማራ ልማት ማህበር ይገኙበታል፡፡

 

 

Read 4197 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:27