Saturday, 17 November 2018 11:25

“ሱቱኤል” በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


     በታገል አምሣል የተፃፈው “ሱቱኤል - የምስጢራዊቷ ምድር ትንሣኤ” የተሰኘው መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
የልሳን ግእዝ መምህርና ደራሲ ዐቢይ ለቤዛ “ከሌላ ዕይታ” በሚል ርዕስ ስለመጽሐፉ በሰጡት አስተያየት፤ “ፅሁፉ በፖለቲካና ምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ለወደቁና መካከል ላይ ላሉት ሀገሮች ሁነኛ የለውጥ ቁልፍ አመላካች ነው… የአዕምሮ ሀብት አጠቃቀም፣ የዕውቀት አረዳድና አተገባበር የሚያስከትለውን ውጤትም በተሻለ ትኩረት እንዲቃኝ ያደርጋል” ብለዋል፡፡
በ285 ገፆች የተቀነበበው “ሱቱኤል”፤ ለአገር ውስጥ በ132 ብር፣ ለውጭ አገራት በ27 ዶላር  ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 4385 times