Saturday, 03 November 2018 16:04

ኢነትረኔት እኔ የወሲብ ፍላጎት/ ባህሪ በወጣትነት

Written by  አዲሱ ደረሰ ከኢሶግ
Rate this item
(3 votes)

  እንደምን ሰነበታችሁ ውድ የላንቺና ላነተ አንባቢዎች፡፡ በዛሬው አምዳችንበወጣቱ ላይ ስለሚስተዋለው የኢንተርኔት አጠቃቀም እና ይህም በወሲብ ፍላጎት እና ባህሪው ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ አንዳንድ መረጃዎችን ልናጋራችሁ ወደናል። ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ያደረግነው በርዕሱ ላይ ተመስርቶ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረቱ አድርጎ በዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰራ አንድ ጥናት ነው፡፡
በወጣትነት ወቅት የሚታየው የወሲብ ፍላጎት ፍጹም ተፈጥሯዊና በተለያዩ የህይወት ልድ እና ተጋላጭነት እየዳበረ የሚመጣ ነው፡፡ በቅርቡ በአገራችን እየተስፋፋ የመጣው የኢንተርኔት አገልግሎት ደግሞ አንዱ የወጣቱ ተጋላጭነት ጠንክሮ የሚተዋልበት እውነታ ነው፡፡ ለዛሬ መነሻ ያደረግነው ጥናት ይህ አገልግሎት በወጣቱ የወሲብ ፍላጎትና ባህሪ ላይ ያለውን ተጽዕኖ ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡
የወሲብ ፍላጎትና ባህሪያትን ማስተዋል እና ለስሜቶቹም መልስ ለመስጠት የሚደረግ ትግል የማንኛውም እድሜው 16-24 ዐመት ያለ ወጣት ላይ የሚስተዋል ባህሪ ነው፡፡
አንደ ኢትዮጲያ ባሉ አገራት እና ስለወሲብ ባህሪያት ወጣቶች በግልጽ ከቤተሰብ ጋር መወያየት እምብዛም ባዳበረባቸው አገራት ውስጥ ወጣቶች ወደግዑዙ ሚዲያ እና ወደጓደኞቻቸው እንደሚያዘነብሉ ጥናቱ ያስታውሳል፡፡
በ2012 በትምህርት ሚኒስቴር የተሰራ ጥናትን መሰረት አድርጎ የጥናት ወረቀቱ እንደሚያስቀምጠው በኢትዮጲያ አንድ በመቶ የሚሆነው ህዝብ የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛል። ሰላሳ በመቶ የሚሆነው ደግሞ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ 19 በመቶ የሚሆነው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እንደሆነ ወረቀቱ ያስነብባል፡፡
ብዙ ጊዜ ወጣትነት አዳዲስ ነገሮችን ለመጠቀም ያለ ከፍተኛ ጉጉት የሚያድርበት የእድሜ ክልል ያርገዋል- ወጣትነትን፡፡ ይህ ባህሪም ወጣትነትን ለአዳዲ የቴክኖሎጂም ሆነ ህጻንነትን ሲሻገሩ የሚመጣን የወሲብ ፍላጎት ለማወቅ የሚኖር ከፍተኛ ጉጉት የሚኖርበት የእድሜ ክልል ያደርገዋል፡፡ እዚህ ቦታ ላይ ነው እንግዲህ ወጣትነት፤ የኢንተርኔት አጠቃቀም እና የወሲብ ፍላት የሚገናኙበት ቦታ- እንደጥናቱ፡፡
ለጥናቱ ጥያቄ ከቀረበላቸው ተማሪዎች መካከል 33 በመቶ የሚሆኑት ለጠቅላላ እቅቀት የሚሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት ኢንተርኔትን እንደጠሚጠቀሙበት ሲናገሩ 26 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ለመዝናኛነት ይጠቀሙበታል፡፡
ኢንተርኔትን ለመዝናኛነት ከሚጠቀሙበት ተማሪዎች መካከል ደግሞ 33 በመቶ የሚሆኑት ለማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ሲጠቀሙበት፤ 14 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ወሲባዊ ፊልሞችን እና ምስሎችን ለማየት እንደሚጠቀሙበት ያወሳል። በጥናቱ ከተሳተፉ ተማሪዎች መካከል 31 በመቶ የሚሆኑት ኢንተርኔትን ብቻቸውን ሲሆኑ መጠቀምን እንደሚያዘወትሩ ሲናገሩ ከነዚህ መካከል 53 በመቶ የሚሆኑት ማታ አልጋቸው ላይ ጋደም ብለው መጠቀምን እንደሚያዘወትሩ ተናግረዋል፡፡
የጥና ጸኃፊ አነጋገርኳቸው ካቻቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጠቅሳ እንደምታብራራው ከሆነ ተማሪዎች ኢንተርኔትን የወሲብ ፍላጎታቸውን ለማርካትም ሆነ ወሲባዊ ባህሪያትን ለማጥናት እንደሚጠቀሙበት ታስቀምጣለች። እንደተማሪዎቹ ከሆነ ኢንተርኔት ወሲባዊ ባህሪያትን ለማጥናት እና በተቃራኒ ጾታ ባላቸው እኩዮቻቸው ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚያስችሉ ዘመን አመጣሽ ባሪያትን እንዲተዋወቁ ይረዳናል ብለው ያምናሉ፡፡
ተቀባይነት ያለው ወሲባዊ ባህሪ የሚባሉት በምዕራባውያ እየተሰሩ የሚከፋፈሉትን እና በገሚስ ግልጽ እና ሙሉ በሙሉ ግልጽ የሆኑ ወሲባዊ ፊልችን እንደሆነ ጥናቱ ያስቀምጣል፡፡
ጥናቱ አነጋገርኩት ያለውን አንድ መምህር ጠቅሶ እንደሚያስቀምጠው እነዚህን ፊልሞች በትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥም ለመከልከል አለመቻሉን ይገራል፡፡ ለዚህ ምክኒያቱ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢከለከሉም ወላጆቻቸው በቤት ውስጥ አነዚህን ፊልሞች ለማየት የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎችን ስለፈጠሩላቸው ትርፉ ልፋት ነው የሚል ስሜት በትምህርት ቤቶች ዘንድ እንደፈጠረም ያብራራል፡፡
ተማሪዎች በተጨማሪም ኢንተርኔትን ከተቃራኒ ጾታ ጋር ግንኙነትን ለመፍጠር እንደሚጠቀሙበትም ይጠቁማል፡፡ እነዚህም 21 በመቶ ይሆናሉ ይላል፡፡ ከነዚህም መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት በኢንተርኔት ከተዋወቁት የተቃራኒ ጾታ ግለሰብ ጋር ወሲብ መፈጸማቸውን ተናግራዋል ይላል፡፡ አሁን ባለበት ደረጃ ቁጥሩ አስደንጋጭ ባይባልም እድሚያቸው ከ15-17 የሚሆናቸው ወጣቶች ሳይቀር በማበራዊ ድህረ ገጽ ላይ ብቻ ከሚያውቁት/ ቋት ግለሰብ ጋር ወሲብ ፈጽመው እንደሚያውቁ ይናገራል፡፡ ይህም ግኝቴ የማህበራዊ ትስስር ድህረ ገጾች በዋናነት ወደ ወሲባዊ ግንኙነት ድህረ ገጽነት እየተቀየሩ ስለመሆኑ BBC ከሰራው ዘጋቢ ፊልም ጋር ተደጋጋፊ ነው ይላል ጥናቱ፡፡
ጥናቱ በማጠቃለያውም ወጣ በኢንተርኔት ምክኒት ለተሳሳተ እና ጎጂ ለሆኑ መረጃዎች ከመጋለጡም ባለፈ በኢንተርኔት ለሚፈጸም የስብዕና ማጉደፍ /ቡሊይንግ/ እየተጋለጠ እንደሚገኝ፤ እውነተኛ ላልሆነ/ አስመሳይ የፍቅር ግንኙነቶች እራሱን አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ ደርሼበታለው ይላል፡፡ ኢንተርኔት መረጃን ለማግኘት እጅግ ቀላል እንደማድረጉ የተገኘው መረጃ ሁሉ ተዐማኒ እንደሆነ የሚያስመስለው ገጽታው ግን ወጣቱን ወዳልሆነ ወሲባዊ ባህሪ እንዳይመራው ስጋት አለኝ ይላል ጥናቱ፡፡ መልካም ሳምንት፡፡

Read 3992 times