Saturday, 20 October 2018 14:07

የህጻናት ያልተመጣጠነ ምግብ አሳሳቢነት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

በአለም አቀፍ ደረጃ እንደውጭው አቆጣጠር በ2000-20017 ድረስ እድሜያቸው ከ5/አመት በታች የሆኑ ባልተመጣጠነ ምግብ ምክንያት እድገታቸው አዝጋሚ ሕጻናት ቁጥር ከ/198/ሚሊዮን ወደ /151/ ሚሊዮን ዝቅ ብሎአል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በመካ ከለኛው እና ምእራብ አፍሪካ ባልተመጣጠነ ምግብ ምክንያት እድገታቸው የተዛባ ህጻናት ቁጥር ከ22.8/ሚሊዮን ወደ 28.9/ሚሊዮን ጨምሮአል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በ2017/ /22.2/ % የሚሆኑ ከ5/አመት በታች ያሉ ሕጻናት ከአራቱ አንዱ ባልተመጣጠነ ምግብ ምክንያት እድገታቸው አዝጋሚ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ከ2000-2017/ ከ/32.6/% ወደ /22.2/ % ማለትም ከ198/ሚሊ ዮን ወደ /151/ሚሊዮን ዝቅ ብሎአል፡፡ ችግር ካጋጠማቸው ሕጻናት ከሶስቱ አንዱ የሚገ ኘው ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት መሆኑ ተጠቁሞአል፡፡
ከ5/አመት በታች የሆኑ ሕጻናት ሞት ግማሽ ያህሉ በተመጣጠነ ምግብ ጉድለት ምክንያት መሆኑን May/2018/የወጣ የዩኒሴፍ ፤የአለም የጤና ድርጅትና የአለም ባንክ በጥምረት ያወጡት መረጃ ያሳያል፡፡  በተመጣጠነ ምግብ ጉድለት ምክንያት በአመት 3/ሚሊዮን ያህል ሕጻናት በአለማችን ለህልፈት ይዳረጋሉ ፡፡ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ሕጻናቱን ለሞት የሚዳርገው በተለያዩ ኢንፌክሽኖችና ለእርዳታውም የሚኖረው መዘግየት ተዳምሮ ነው፡፡
የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ኢንፌክሽን ያላቸው ጥምረት የሕጻኑን የአካል እድገቱን ከመፈታተኑም በላይ ለማያቋርጥ ሕመም ስለሚዳርገው ምግብ የመውሰድ አቅሙን ሁሉ ሊፈታተነው ይችላል፡፡ ሕጻኑ በተወለደ የመጀመሪያዎቹ /1000/አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ የሚታይ የሰውነት መቀጨጭ ከመኖሩም በላይ ልጁ ቢያድግ እንኩዋን የመማርና የመስራት ችሎታው ላይ ጉድለት ያስከትላል፡፡
እንደውጭው አቆጣጠር በ2018/ የወጣው መረጃ እንደታየው ከሆነ በምግብ አለመመጣጠን ምክንያት አካላቸው የተጎዳ ልጆች ቁጥር ከ2000/ዓ/ም ጀምሮ የቀነሰ ሲሆን ይኼውም ከ4/ ልጆች አንድ ያህል ማለትም በአለም ላይ 151/ሚሊዮን ያህል ከ5/አመት በታች የሆኑ ህጻናት ሰውነታቸው በምግብ እጥረት ምክንያት የተጎዳ ሆኖ ተመዝግቦአል፡፡ ወደ 51/ ሚሊዮን ያህል ልጆች ደግሞ ቀስ በቀስ በሕመም እየተጎዱ መጠናከር ሲያቅታቸው ወደ ሕልፈትም ያመሩ ቀላል ቁጥር የላቸውም፡፡ በተያያዘም መረጃው እንደሚጠቁመው በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ክብደታቸው ከመጠን ያለፈ ልጆች ቁጥርም ላለፉት አስርት አመታት ለውጥ ያላሳየ እና አስጊ መሆኑን የዩኒሴፍ መረጃ ያሳያል፡፡
በአለማችን ልማትን በማፋጠኑ ረገድ ትኩረት እንዲሰጠው ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የህጻናቱ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ነው፡፡ ከ2015/ በሁዋላ ያለው የልማት ሁኔታ ምናል ባትም አለም ያለችበትን የህጻናት ምግብ እጥረት ቀንሶ በትክክለኛው አካሄድ ላይ ትሁን አት ሁን የሚያሳይና በተለይም በምእተ አመቱ የልማት ግብ ቁጥር /2/ ላይ ረሀብን ስለማስወገድ እና የምግብ ዋስትናን ስለማረጋገጥ እንዲሁም የህጻናቱን አመጋገብ ለማሻሻል እንዲያስችል ቀጣይነት ያለውና አስተማማኝ የሆነ የግብርና ተግባርን መፈጸም አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሞ አል፡፡  
የፓን አፍሪካን ሜዲካል ጆርናል እንደሚገልጸው የምግብ ዋስትና በተለይም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ያልተሙዋላ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አለም አቀፉ የአየር ጸባይ ለውጥ ፤ምግ ብን በትክክል በሁሉም ቦታ በተመጣጠነ መንገድ የማዳረስ ችግር ፤ውጤታማ የሆኑ የግብርና ውጤቶች አለመኖር፤እና በየሀገራቱ ያሉ አመራሮች ከሚያሳዩት የአስተዳደራዊ ስራ መዛባት… ወይም ጉዳዩን በሚመለከት ፍላጎት ማጣት ወዘተ… መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ከዚህም በላይ ውስብስብ የሆኑ እና ብቃት እንዲሁም ቅንጅት በጎደላቸው አለምአቀፍ ምላሾችም ችግሩ ሊከሰት እንደሚችል ፓን አፍሪካ ይጠቁማል፡፡ ስለዚህም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶች የምግብ ዋስትና እንደማ ይኖራቸው እና በተለይም ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ፤ እርጉዝ ሴቶች፤ ሕመም የገጠማቸው፤ ስራ ለማግኘት ከቦታ ቦታ የሚሰደዱ፤ በከተሞች የሚኖሩ እድሜያቸው የገፋ ሰዎች፤ እና ከ5/አመት በታች የሆኑ ሕጻናት ይበልጥ ለምግብ እጥረቱ ተጋላጭ ናቸው፡፡  
የሀገራቱን ግብርና ማሳደግ…የአየር ሁኔታውን አስቀድሞ ማወቅ የሚቻልበትን መንገድ ማሳ ደግ፤ ለልማት እና መሰረታዊ ነገሮች መሟላት የሚረዳ የገንዘብ እርዳታ ማድረግ እንዲሁም ሀገራት ይበልጥ መገናኘትና ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር ማድረግ ከሰሐራ በታች ላሉ ሀገራት ቀጣይነት እና በተግባር የሚታይ የምግብ ዋስትና እንዲኖርና የወደፊት ሕይወታ ቸውን ለማስ ተካከል ያስችላል፡፡ በተጨማሪም የተጠቀሱት ድርጊቶች እውን ከሆኑ ሀገራቱ በውጭ ምግብ ላይ የሚያደርጉትን ጥገኝነት እንደሚቀንስላቸው እና በተለይም ከ5/አመት በታች ያሉ ሕጻናት በአገር ውስጥ የተመረቱ ምግቦችን መመገብ ይችላሉ፡፡
የህጻናቱን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሁኔታ  በኢትዮጵያም አንድ ትልቅ ችግር ሆኖ የሚታይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ወደ /2.7/ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለችግር የሚ ዳረጉ ሲሆን ምክንያታቸውም …
ሰዎች በቋሚነት ማግኘት የሚገባቸውን ምግብ በሰው ሰራሽ ወይንም በተፈጥሮ …ድርቅ…. በመሳሰሉት ምክንያቶች በሚደርስ ችግር ማግኘት አለመቻላቸው፤
ወይንም ማግኘት የሚገባቸውን ምግብ በቀጥታ በራሳቸው መንገድ ሳይሆን በተወሰነ ጊዜ በእርዳታ እህሉን ወይንም መግዣ ገንዘቡን ጠብቀው የሚቀበሉ ሲሆን ነው፡፡
እንደ USAID ዘገባ በኢትዮጵያ /44/በመቶ የሚሆኑት ባልተመጣጠነ ምግብ ምክንያት ለችግር የሚዳረጉት በእድሜያቸው ከ5/አመት በታች ያሉት ሲሆኑ እነዚህም አዝጋሚ የሆነ የእድገት ችግር የሚደርስባቸው ናቸው፡፡ የአለም የምግብ ድርጅት ዘገባ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ካለው አጠቃላይ የምግብ እጥረት /81/% ከሆነውና መፍትሔ ካልተሰጠው ውስጥ 28/% የሚሆነው ከ5/አመት በታች ባሉ ህጻናት ላይ በየአመቱ የሚታይ ነው፡፡
ጨቅላ ሕጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሲገጥማቸው በሕይወት ዘመን ሁሉ የማይፈታ ችግር ይዘው ሊዘልቁ እንደሚችልና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያደጉ ልጆች በትምህርት አቀባበላቸው ደካሞች እንዲሁም በስራ ትጋታቸው ወደሁዋላ የሚቀሩ ናቸው፡፡ እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ወደ /16/% የሚሆኑት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ላይ የሚገኙ የችግሩ ሰለባዎች ናቸው፡፡
የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በኢትዮጵያ የሚሊዮኖችን ሕይወት አደጋ ላይ መጣል ብቻ ሳይሆን የአምራቹን ኃይል አቅምና ብቃት ስለሚፈታተን ሀገሪቱ ከድህነት እንዳትወጣም ያደርጋታል፡፡ የህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በኢትዮጵያ ወደ 5.5/ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስ ከትል እና ይህም በመቶኛ ሲሰላ ወደ /16.5/% እንደሚሆን ይገመታል፡፡
ይህ የህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምን ያህል በአገር ላይ ተጽእኖ እንደሚያስከትል የኢትዮጵያ መንግስት በመረዳቱም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በተለይም June/2013/ በወጣው ብሔራዊ የስነምግብ ፕላን ላይ በዚህ ምክንያት የሚደርሰውን ችግር ለመቀነስ አስከፊውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መቀነስ ፤ በሴቶች ላይ በተለይም በመዋለድ እድሜ የደረሱትን ከችግሩ መከላከል በመሳሰሉት ላይ እቅድ ተይዞአል፡፡ ኢትዮጵያ በምግብ እጥረት ሕጻናቱ እንዳይሰቃዩ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ እንዳለች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ወላጅ እንዲሁም አሳዳጊዎች ጨቅላ ሕጻናቱንም ሆነ ታዳጊዎችን በተገቢው መንገድ አገር በቀል ከሆኑት ጀምሮ አቅም እንደፈቀደ የተመጣጠነ ምግብ መስጠት ለህጻናቱ ብሎም ለህብረተሰቡ እንዲሁም በአገር ደረጃ ለሚኖረው እድገት ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ከባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ማግኘት ጠቃሚ መሆኑን አምዱ ይጠቁማል፡፡

Read 1781 times